Saturday, 02 April 2022 11:36

“አባይ” የተሰኘ ህብረ ዝማሬ ሀሙስ በጎንደር ይመቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   የአባይን ወንዝ እና  በወንዙ ዙሪያ ኢትዮጵያ ከበፊት ጀምሮ የሚገጥማትን ፈተና፣የአባይ ወንዝ ለሰው ስልጣኔ ያለውን ፋይዳና በአጠቃላይ በአባይና በአባይ ዙሪያ ያሉ በረከቶችንና ተግዳሮቾችን መሰረት አድርጎ የተሰናዳው “አባይ” ህብረ ዝማሬ ሀሙስ  መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ይመረቃል፡፡
በሙዚቃ ባለሙያው ገብረማርያም ይርጋ ግጥምና ዜማው ተሰርቶ በጎንደር ፋሲለደስ የኪነት ቡድን የተዘመረው ይኸው ህብረ ዝማሬ፣ በአበጋዝ ክብረ ወርቅ ሺዎታ ቅንብሩ የተሰራለት ሲሆን በክብር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ፕሮዲዩስ መደረጉን የህብረ ዝማሬው ግጥምና ዜማ ደራሲ የሙዚቃ ባለሙያ ገብረማሪያም ይርጋ ተናግሯል፡፡ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የህብረ ዝማሬው ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር ሲሆን፣ ቀረፃና ኤዲቲንጉ የአርቲስት አምለሰት ሙጬ ኩባንያ በሆነው “ማያ ፊልም ፕሮዳክሽን” መሰራቱም ታውቋል፡፡
ህብረ ዝማሬው በጎንደር ዩኒቨርስቲ አጋፋሪነት በጎንደር ከተማ በድምቀት ይመረቃል የተባለ ሲሆን በእለቱ ቴዲ አፍሮን ጨምሮ በህብረ ዝማሬው ስራ ላይ የተሳተፉ ከያንያንና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ  አመራሮች ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅ ገብረማርያም ይርጋ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡


Read 41303 times