Monday, 04 April 2022 00:00

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአለማቀፍ ደረጃ ተባብሷል ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  የአለማችን መንግስታት ባለፈው የፈረንጆች አመት 2021 የመናገርና የመሰብሰብ መብቶችን ጨምሮ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች በከፍተኛ ሁኔታ መጣሳቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሞኑ ይፋ ያደረገው አመታዊ አለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት አመልክቷል፡፡
ባለፈው የፈረንጆች አመት 2021 ብቻ 67 የሚሆኑ የአለማችን አገራት የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነትን የሚጋፉ አዳዲስ ህጎችን ማውጣታቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ በአሜሪካ ብቻ ከ80 በላይ መሰል ህጎች መውጣታቸውንም በአብነት ጠቅሷል፡፡
ተቋሙ በ154 የአለማችን አገራት ላይ ያደረገውን ጥናት መሰረት አድርጎ ያወጣው አመታዊ ሪፖርት፣ የተቃዋሚዎችና የጋዜጠኞች ድብደባና የጅምላ እስር፣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ያለአግባብ መታሰር፣ የማህበራዊ ድረገጾች መዘጋትና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በአመቱ በአገራት መንግስታት በስፋት የተፈጸሙ ዋነኛ የመብት ጥሰቶች መሆናቸውንም አመልክቷል፡፡
ቻይና እና ኢራንን በመሳሰሉ አገራት መንግስታት ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ትችት የሰነዘሩባቸውን ግለሰቦች በብዛት ማሰራቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ወረርሽኙን ለመከላከል በሚል ሰበብ የተቃውሞ ሰልፎችን የከለከሉ መንግስታትም በርካቶች እንደሆኑ አስታውቋል፡፡

Read 4362 times