Saturday, 09 April 2022 13:18

ባለፉት 2 ወራት ከ32 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ተሰደዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ባለፉት 2 ወራት ብቻ በአማካይ 32 ሺህ 270 ያህል ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ ሀገራቸውን ጥለው ወደ መካከለኛው ምስራቅ  ሀገራት መሰደዳቸውን አለማቀፉ የስደተኞቸ ድርጅት (አይኦኤም ) ትናንት ባወጣው ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ከሊቢያ ተነስተው ወደ አውሮፓ ሲጓዙ የነበሩ ስደተኞች መካከል 57ቱ መሞታቸው ተገለጸ። - የቫቲካን ዜና
የመን እና ኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ ስደተኞች የሚንቀሳቀሱባቸው ሀገራት መሆናቸውን ያመለከተው አለማቀፍ የስደተኞች ድርጅት ሪፖርት፤ አዲሱ የፈረንጆች አመት ከገባ ወዲህ በጥርና የካቲት ወር ብቻ ከምስራቅ አፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ  ሀገራት በአማካይ ኢትዮጵያ እና የመን በርካቶች የተሰደዱባቸው ሀገራት ሆነዋል፡፡
በኢትዮጵያ በየካቲት ወር 2014 ብቻ 15 ሺህ 729  ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ሀገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን  ሪፖርቱ ያመለክታል  በየካቲት ወር በህገ ወጥ መንገድ ሀገራቸውን ጥለው ከተሰደዱ ዜጎች መካከል 37 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ከኦሮሚያ ክልል ሲሆን ፣26 በመቶ ከአማራ፣16 በመቶ ከደቡብ፣ 2 በመቶ ከትግራይና የተቀሩት ከሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች መሆናቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡
ከስደተኞቹ መካከል 64 በመቶ ወንዶች ፣30 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው። 6 በመቶ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች ሲሆን ከእነዚህም 4 በመቶዎቹ ወንዶች እንዲሁም 2 በመቶዎቹ ሴቶች መሆቸው በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡BBC News Amharic - መቶ አምሳ ስደተኞች በሊቢያ ዳርቻ መስመጣቸው ተገለፀ  ---------------------------------------------------------- በሊቢያ ዳርቻ 150  ስደተኞች በጀልባ እየተጓዙ ባለበት ወቅት መስመጣቸውን የተባበሩት መንግሥት ...
ከአጠቃላይ ስደተኞቹ መካከል 60 በመቶዎቹ መዳረሻቸው ሳውዲ አረቢያ ሲሆን ፣23 በመቶዎቹ ለመሸጋገሪያነት የሚጠቀሟትን ጅቡቲ መድረሻቸው አድርገዋታል። 6 በመቶዎቹ ደግሞ መዳረሻቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በዘንድሮ ጥር እና የካቲት  ወር ብቻ 32 ሺህ 270 ዜጎች ከኢትዮጵያ መሰደዳቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ከተቀመጠችው የመን 14 ሺህ 298 ሰዎች መዳረሻቸውን ሳውዲ አረቢያ በማድረግ ተሰደዋል፡፡
ባለፉት 2 ወራት መነሻቸውን የመን በማድረግ ወደ ሳውዲ አረቢያ ከገቡ ስደተኞች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ነው ሪፖርቱ ያመለከተው፡፡


Read 10255 times