Friday, 15 April 2022 16:37

የቀልድ ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አንድ ቄስ  ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ወደሚገኝ የወንዶች ፀጉር ቤት ይሄዱና፣ ፀጉራቸውን ይስተካከላሉ። ሲጨርሱም ምን ያህል መክፈል እንዳለባቸው ይጠይቃሉ።
 “አባት ክፍያ የለውም” ይላል ፀጉር አስተካካዩ፤ “ይሄንን ለፈጣሪዬ እንደማበረክተው አገልግሎት ነው የምቆጥረው።” ሲልም ያክላል።
በነጋታው ታዲያ ፀጉር አስተካካዩ ሥራ ቦታው ሲደርስ፣ ከቄሱ ትናንሽ የፀሎት መፃህፍትና የምስጋና መልዕክት ተቀምጦለት አገኘ፡፡
ከጥቂት  ቀናት በኋላ ደግሞ አንድ የፖሊስ መኮንን፣ ወደ ፀጉር ቤቱ ጎራ ይልና ፀጉሩን ይቆረጣል። ከዚያም “ምን ያህል ልክፈል?” ሲል ይጠይቃል።
“በነፃ ነው ጌታዬ; ፀጉር አስተካካዩ ይመልሳል፤ #ይሄንን ለማህበረሰቤ እንደማበረክተው አገልግሎት ነው የምቆጥረው።”
 በነጋታው ጸጉር አስተካካዩ ወደ ሥራው ሲገባ፣ ከፖሊሱ በርከት ያሉ ጣፈጭ ዶናቶችና የምስጋና መልዕክት ተቀምጦ ጠበቀው።
ጥቂት ቀናት ቆይቶ ደግሞ አንድ ሴናተር ፀጉሩን ሊቆረጥ ይመጣል። ከተቆረጠም በኋላ “ስንት ልቀጣ?” ሲል እየቀለደ ይጠይቃል።
“ክቡር ሴናተር ክፍያ የለውም” ይመልሳል ፀጉር አስተካካዩ፤ “ይሄንን ለአገሬ እንደምሰጠው አገልግሎት ነው የምቆጥረው።”
በነጋታው ጠዋት ፀጉር ቤቱ በር ላይ ደርዘን የሚያህሉ ሴናተሮች ተኮልኩለው፣ ጸጉር አስተካካዩን  ሲጠብቁት ነበር ያገኛቸው - በነፃ ጸጉራቸውን ለመቆረጥ።


Read 2314 times