Saturday, 16 April 2022 13:28

“ፋሲካ በመቻሬ” የንግድ ትርኢትና ባዛር ተከፍቷል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

      ከ200 በላይ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው ቀርበዋል
                       
              በሜላ ኢቨንትስ የተዘጋጀውና “ፋሲካን በመቻሬ” የተሰኘው የንግድ ትርኢትና ባዛር ከትናንት በስቲያ ሀሙስ በመቻሬ ሜዳ በድምቀት ተከፈተ። እስከ ሚያዝያ 15 ቀን በሚቆየው በዚህ የንግድ ትርኢትና ባዛር፤ ከ200 በላይ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ይዘው መቅረባቸውም በመክፈቻው ላይ ተገልጿል።
በንግድ ትርኢቱ የፈርኒቸር ውጤቶች፣ የቆዳ አልባሳት፣ ለበዓሉ የሚያሥፈልጉ እንደ እንቁላል፣ ዶሮ፣ ዱቄትና መሰል የፍጆታ ምርቶች ለማህበረሰቡ መቅረባቸው የተጠቆመ ሲሆን ከባዛር ውጪም ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ በማቅረብ የሚታወቁት እንደነ ኩይንስ ሱፐር ማርኬት፣ በሽ ገበያ እና ኤልፎራ ያሉ ድርጅቶችን ጨምሮ በርካቶች ተሳታፊ መሆናቸውም ታውቋል፤ በተንጣለለው የመቻሬ ሜዳ የመኪና ማቆምያም ሆነ የጥበቃ ችግር እንደሌለ የገለጹት አዘጋጆቹ፤ የህፃናት መጫዎቻዎችና፣ መዝናኛዎች እንዲሁም በየቀኑ የሙዚቃ ኮንሰርት እየቀረበ ለ15 ቀናት በድምቀት እንደሚቀጥል ተነግሯል።
ከሙዚቀኞች ያሬድ ነጉ፣ ለምለም ኃ/ሚካኤልና ሳሚ ዳንን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ድምፃውያንና የከተማችን እውቅ ዲጄዎች በስራዎቻቸው ጎብኝውን ያዝናኑታል ተብሏል።  

Read 1213 times