Print this page
Saturday, 16 April 2022 13:57

በደቡብ ኦሞ ዞን ለተፈጠረው ችግር መንግስት አፋጣኝ እልባት እንዲሰጥ ኢሰመጉ አሳሰበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  በተለያዩ ወረዳዎች ከ150 በላይ መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል
                               
           “ራሳችንን ችለን ዞን እንሁን” ከሚል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በደቡብ ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ደቡብ አሪ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌያት የተፈጠረው የፀጥታ ችግር አስጊ መሆኑን  የጠቆመው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)  ችግሩ ተባብሶ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት መንግስት እልባት እንዲያበጅለት አሳስቧል፡፡
በደቡብ አሪ ዞን ወረዳ ውስጥ በሚገኙ በሊጠር፣ ሺሸር፣ ሆለታ፣ በርካማማ እና ቲቲ ቀበሌዎች ውስጥ ከመጋቢት 28 ቀን 2014 እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2014 ድረስ ቤቶችን በማቃጠል፣ንብረት በማውደምና ዘረፋ በመፈጸም የአሪ ወጣት ነን የሚሉና ራሳቸውን “ሽኮን” በሚል ስያሜ ያደራጁ ቡድኖች ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ብሏል በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ።
የአካባቢው አስተዳደር በበኩሉ ባጋራው መረጃ፤ የዞኑ ዋና ከተማ ጂንካን ጨምሮ በተለያዩ ወረዳዎች ከ150 በላይ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን አስታውቋል፡፡
የግጭቱ መነሻ የሆነው የአሪ ወረዳ የዞን አደረጃጀት ጥያቄ፣ ለደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፣ “የዞኑ ም/ቤት ጉዳዩን ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ም/ቤት አላስተላለፈልንም” በሚል ችግሩ መፈጠሩን ኢሠመጉ አመልክቷል፡፡ በዚህ ሰበብም በዞኑ በሚኖሩ ሠላማዊ ዜጎች ሃብትና ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት የከፋ መሆኑን የጠቀሰው የኢሠመጉ ሪፖርት፤ መንግስት አጥፊዎችን አጣርቶ ለህግ እንዲያቀርብ፣ በአካባቢው ላሉ ዜጎች የህይወት ዋስትና እንዲሰጥም ጠይቋል-በሪፖርቱ፡፡



Read 10962 times
Administrator

Latest from Administrator