Print this page
Monday, 18 April 2022 00:00

ባይደንን ክፉኛ የዘለፉት ትራምፕ በቀጣዩ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ተናገሩ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ በኖርዝ ካሮሊና ሴልማ ከተማ በተካሄደ ሰልፍ ላይ ባደረጉትና የወቅቱን የአገሪቱ መሪ ጆ ባይደንን ክፉኛ በዘለፉበት ንግግራቸው፣ በ2024 በሚካሄደው ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ጆ ባይደን በተለይ ከሩስያና ዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ አገራችንን ያዋረዱ ሰው ናቸው ሲሉ በአደባባይ የዘለፉት የ75 አመቱ ትራምፕ፤ የጤናቸው  ጉዳይ ካላሰጋቸው በምርጫው ሊወዳደሩ እንደሚችሉ የገለጹ ሲሆን፣ ከተወዳደሩ ግን ለ3ኛ ጊዜ እንደሚያሸንፉ ቅንጣት ታህል እንደማይጠራጠሩ በመናገር፣ በዚያውም ባይደን ባለፈው ምርጫ አላሸነፉኝም የሚለውን አቋማቸውን አጠናክረዋል፡፡

Read 2726 times
Administrator

Latest from Administrator