Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 06 October 2012 12:41

አቶ ከፍያለው አዘዘ አሜሪካ ገብተዋል

Written by 
Rate this item
(4 votes)

የኤጀንሲው ዳይሬክተር በአሜሪካ ሥራ አግኝተዋል

ከአንድ ዓመት በፊት ከምክትል ከንቲባነትና ከማስታወቂያ ቢሮ ኃላፊነት በግምገማ የተነሱት አቶ ከፍያለው አዘዘ እና የግል ተቋማት ሠራተኞች የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው በላይ ከአገር እንደወጡ አለመመለሳቸውን ምንጮች ገለፁ፡፡ ሁለቱም ግለሰቦች አሜሪካን አገር እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከላይ እስከ ታች ተገቢ ያልሆነ ኔትወርክ ዘርግተዋል በሚልና በአቅም ማነስ ተገምግመው ከኃላፊነታቸው የተነሱት አቶ ከፍያለው አዘዘ፤ ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ አሜሪካ እንዳቀኑና ኑሯቸውንም እዚያው ለማድረግ መወሰናቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡

የቀድሞ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የአሁኑ የግል ተቋማት ሠራተኞች የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው በላይም ከመስሪያ ቤታቸው የዓመት ዕረፍት ወስደው እንደወጡ ወደ ስራ ገበታቸው እንዳልተመለሱ ታውቋል፡፡

አቶ ጌታቸው በአሜሪካ ሥራ አግኝተው እንደሄዱ የጠቆሙ ምንጮች እዚህ ሳሉ ሲሰሩ ለቆዩበት መ/ቤት መልቀቂያ እንዳስገቡም ገልፀዋል፡፡

 

Read 3228 times Last modified on Saturday, 06 October 2012 12:48