Print this page
Saturday, 30 April 2022 13:57

"የባለሥልጣናት ምንጣፎች" መጽሐፍ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የጸሐፊ እና ጋዜጠኛ እስክንድር መርሐጽድቅ ሦስተኛ ሥራው የሆነው "የባለሥልጣናት ምንጣፎች እና ሌሎችም አጫጭር እውነተኛ ታሪኮች" መድበል  ተመረቀ፡፡
ባለፈው ሳምንት በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የተመረቀው ይህ መጽሐፍ "የባለሥልጣናት ምንጣፎች" ከተሰኘው በተጨማሪ "መንፈሳውያን ድምጾች"፣ "የተመረጣችሁት እና <የተመረጣችሁት"›፣ "ከብርቄ ሬዲዮ እስከ ፌስቡክ" እና "የሃይማኖት ገበሬው" የተሰኙ የእውነተኛ ታሪክ መድበሎችን ይዟል፡፡  
በምረቃው ላይ የበገና እና የመንዙማ ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን ግጥሞች፣ የጸሐፊው የመገናኛ ብዙኃንና የፌስቡክ ተሳትፎዎች ዳሰሳ ተደርጎባቸዋል፡፡ ከዚህ ሌላ ትውልዱና ሥነ-ምግባር እንዲሁም የአውሮፓ ስፖርት አፍቃሪ ገጠመኝ ቀርቧል፡፡
በርካታ የሥነ-ጽሑፍ ወዳጆች የታደሙበት የመጽሐፉ ምረቃ መግቢያው አንድ ሳንቲም የነበረ ሲሆን ይዘው ለቀረቡ 75 መጻሕፍት፣ ነጻ የቴአትሮች መግቢያ እና የትንሳኤ ሎተሪ ሽልማቶች ተበርክተዋል፡፡
ጸሐፊው በ2005 ዓ.ም. "ቀይ ሥሮች" እና በ2009 ዓ.ም. "ለምን?" የተሰኙ አጫጭር የእውነተኛ ታሪክ መድበሎችን ማሳተሙ ይታወቃል፡፡

Read 11257 times