Friday, 29 April 2022 00:00

ኒው አቢሲኒያ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር ጉባኤውን ዛሬ ያካሂዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በ1996 ዓ.ም የተቋቋመውና በ1997 ዓ.ም ስራ የጀመረው “ኒው አቢሲኒያ ኮሌጅ” ዛሬ ከረፋዱ 3፡30 ጀምሮ በኮሌጁ አዳራሽ የጥናትና ምርምር ጉባኤውን ያካሂዳል። ኮሌጁ ከሚያከናውናቸው የመማር ማስተማር ስራዎቹ ጎን ለጎን የጥናትና ምርምር ስራዎችንና የማህበረሰብ አቀፍ አገልሎቶችን በመስጠት የተቋቋመበትን ዓላማ በአግባቡ የሚመራ ሲሆን ችግር ፈቺና ለማህረሰብ ልማት የሚውሉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በመስራትም ሃላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን የኮሌጁ ሃላፊዎች ተናግረዋል።
በዛሬው እለትም “Job creation and employment unemployement in Ethiopia”፣ “Determinants of foreign direct invesment inflows in Ethiopia” እንዲሁም “Higher education Program level quality assurance” በተሰኙ ርዕሶች ላይ የጥናትና ምርምር ጉባኤውን እንደሚያካሂድ የኮሌጁ ስራ አስኪያጅ አቶ አቶ ደረጀ ምንላርግህ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል። በጉባኤው ላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ፣ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት  ይካሄዳል ተብሏል። ኒው አቢሲኒያ ኮሌጅ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በዲግሪ ፕሮግራም፣ እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፎች በርካታ ተማሪዎችን በማብቃት ለየዘርፉ የተማረ የሰው ሀይል በማፍራት ግንባር ቀደም ኮሌጅ ስለመሆኑም ስራ አስኪያጁ ጨምረው ገልጸዋል።

Read 11371 times