የሚሰዋ ፍቅር
ፍሬ ዛፍ ላይ እያለኮ፤ ቢበስልም እዚያው ላይ አይበላም
ፍሬ መልቀም የምንለው -
ሥራ እንዳለ ስናውቅ ነው፡፡
ምክንያቱም፡-
ያለ ስራ ፍሬ የለም
ያለ ስቅለትም ትንሳኤ
ያለ ትንሳኤም ስርየት
የስጋ ወደሙ ብስራት፡፡
በሂደት ነው ፍሬ ‘ሚበስል
እዛፍ ላይ አይበላም፡፡
ፍሬ በስሎ የሚበላው፡-
ወይ ራሱ በስሎ ሲወድቅ፤
ወይ እኛ ስንለቅመው ነው፤
አልያ ወድቀን መጠበቅ ነው፡፡
ትንሳኤ አይወድቅም ግና
የመስዋዕት ልብ ላለው
የሚሰዋ ፍቅር ላለው!
ትንሳኤ ሁሌ አይቀሬ ነው፡፡
(ነቢይ መኮንን፤ ግንቦት 2012 ዓ.ም)