Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 06 October 2012 13:14

“ስሌት” ፊልም ነገ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በሱራፌል ኪዳኔ ተደርሶ በታጠቅ ኃይለማርያም እና ሱራፌል ኪዳኔ የተዘጋጀው “ስሌት” ፊልም ነገ በብሔራዊ ትያትር ይመረቃል፡፡ በአሻራ ፊልምስ የተዘጋጀውና 23 ተዋንያን እንደተሣተፉበት የተገለፀው ይኸው ፊልም ለየት ያለ ዘውግን ይዞ የተሠራና ከ13 ዓመት በታች ዕድሜ ላላቸው ታዳጊዎች ማየት የተከለከለ እንደሆነ አዘጋጆቹ ከትናንት በስቲያ በሲዮናት ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡
አዲስ አበባንና አዳማ ከተማን መቼት አድርጐ በተሰራው በዚህ ፊልም ላይ ፍቅርተ ደሳለኝ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ አለምሰገድ ተስፋዬና ሌሎችም አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተውነውበታል፡፡ ፊልሙ የአስራ አንድ ወራት ጊዜንና 582 ሺህ ብር ወጪን መጠየቁን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

Read 2779 times