Print this page
Wednesday, 11 May 2022 00:00

ከ85 በመቶ በላይ የአለም ህዝብ የፕሬስ ነጻነት ጭቆና ተባብሶበታል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

      ሰሜን ኮርያ በፕሬስ ነጻነት ጭቆና አቻ አልተገኘላትም

             ባለፉት 5 አመታት ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው የአለም ህዝብ የፕሬስ ነጻነት ጭቆና እንደተባባሰበትና በመላው አለም 455 ጋዜጠኞች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም ከሰሞኑ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡
ሪፖርተርስ ዊዛውት ቦርደርስ የተባለው የፕሬስ ነጻነት ተሟጋች ተቋም በበኩሉ፤ በ28 የአለማችን አገራት የፕሬስ ነጻነት እጅግ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱንና ከአለማችን አገራት መካከል በፕሬስ ነጻነት ጭቆና ሰሜን ኮርያን የሚፎካከራት እንዳልተገኘ ከሰሞኑ ባወጣው የ2022 የፈረንጆች አመት አለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት ደረጃ ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ተቋሙ በዘንድሮው የፕሬስ ነጻነት ሪፖርቱ ካካተታቸው 180 የአለማችን አገራት መካከል ሰሜን ኮርያ  180ኛ ደረጃን መያዟ የተነገረ ሲሆን፣ ኤርትራ 179ኛ፣ ኢራን 178ኛ፣ ቱርኬሚኒስታን 177ኛ፣ ማይንማር 176ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
አውሮፓዊቷ ኖርዌይ የፕሬስ ነጻነት በእጅጉ ያበበባት የአመቱ ቁጥር አንድ የአለማችን አገር ናት ያለው ሪፖርቱ፤ ዴንማርክ፣ ስዊድን፣ ኢስቶኒያና ፊንላንድን እንደ ቅደም ተከተላቸው እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ሰጥቷቸዋል፡፡
ተቋሙ በጋዜጠኞችና በነጻ ሚዲያ ተቋማት ላይ የሚደርሱ ዘርፈ ብዙ ጥቃትና ጉዳቶችን በመገምገም ባወጣው የዘንድሮው ሪፖርቱ፤ የፕሬስ ነጻነት እጅግ አስከፊ በሆነ ደረጃ ላይ የሚገኝባቸው ብሎ የጠቀሳቸው አገራት 28 ሲሆኑ ይህን ይህል ብዛት ያላቸው አገራት በዚህ ምድብ ውስጥ ሲካተቱ ይህ የመጀመሪያው መሆኑም ተነግሯል፡፡
ቁጥጥር የማይደረግበትና አለማቀፍ ተደራሽነት ያለው የድረገጽ ሚዲያ ለሃሰተኛ መረጃዎች ስርጭትና ፕሮፓጋንዳ መስፋፋት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ መንግስታት በሚዲያ ላይ የሚያደርጉት አፈናም ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክቷል፡፡



Read 8076 times
Administrator

Latest from Administrator