Saturday, 07 May 2022 14:43

” ”ሄሪዮሌ” የሰርግ ዘፈን አልበም እሁድ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ሄሪዮሬ” የተሰኘው የመጀመሪያው የኦሮምኛ የሰርግ አልበም ነገ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል እንደሚመረቅ አዘጋጁ “በሻቱ ቶለማሪያም መልቲ ሚዲያ” አስታወቀ፡፡
“ሄሊዮሌ” በአማርኛ “ጓደኝንት” ማለት እንደሆነ  የተገለፀ ሲሆን ይሄው አልበም ከጥንት ጀምሮ በሰርግና በበዓላት ይዜሙ የነበሩ ግጥምና ዜማዎችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ ብሎም በዘመናዊ መንገድ በማቀናበር በተለያዩ ዘፋኞች የተሰራ ስለመሆኑ መልቲሚዲያው ጨምሮ ገልጿል፡፡
በአልበሙ ላይ ሰባት አንጋፋና አዳዲስ ድምጻውያንም የተሳተፉ ሲሆን 11 ዘፈኖች በውስጡ መያዙም ታውቋል፡፡ ከነዚህ 11 ዘፈኖች መካከል 8ቱ የሰርግ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሶስት ዘፈኖች ደግሞ የልደት፣የምርቃትና የበዓል ዜማዎች መሆናቸውም ታውቋል፡፡
አልበሙ የሰርግ ዘፈን የያዘ እንደመሆኑ በምርቃቱ ዕለት በተለያ ምክንያት ሰረግ መሰረግ  ያልቻሉ 20 ጥንዶችን በማህበራዊ ሚዲያ ጥሪ በማድረግና ሙሉ የሠርግ ወጪያቸውን በመሸፈን ጋብቻቸውን ይፈፅማሉ ተብሏል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ለመታም ቀድመው ከተለዩ የተጋቢዎች ቤተሰበቦች ውጪ ያሉ ሰዎች ምግብ፣መጠጥና የሰርግ አልበሙን ጨምሮ 500 ብር የሚያስከፍለውን ካርድ ከጊዮን መግቢያ በር ላይ በመግዛት መታደም እንደሚችሉም አዘጋጁ በሻቱ ቶለማሪያም መልቲ ሚዲያ ገልጿል፡፡


Read 945 times