Saturday, 07 May 2022 14:45

“የሚዲያ አመራር” መፅሐፍ ረቡዕ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   የእውቁ ጋዜጠኛ መሰለ ገብረህይወት ስራ የሆነው “የሚዲያ አመራር” መፅሐፍ የፊታችነ ረቡዕ ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም  ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ይመረቃል፡፡
መፅሐፉ በዋናነት በሚዲያ አመራር ክፍተት የሚፈጠሩ ችግሮች ያስከተሉትና እያስከተሉ የሚገኙት ችግሮችን በመቅረፍ በትክክለኛ አመራር የሚከናውን ሚዲያን ለመፍጠርና አገርን ለማቅናት መንገድና ሁኔታዎችን ያመለክታል ተብሏል፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በርካታ ጋዜጠኞች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚታደሙ ሲሆን  በዕለቱም በመፅፉ ዙሪያ ዳሰሳ  የተመረጡ የመፅፍ ክፍል ንባብና ሌሎች ኪነ ጥበባዊ ክንውኖች ለታዳሚ እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡


Read 12682 times