Saturday, 07 May 2022 14:53

በ“እረኛዬ” ተከታታይ ድራማ ላይ ሙያዊ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ስላሴ የስነ ጥበባት ማዕከል ተወዳጅ በሆነው “እረኛዬ” ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ዛሬ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ሙያዊ ውይይት እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡
በድራማው መሰረት ላይ ሙያዊ ዳሰሳ የሚያቀርቡት ሰለሞን ተሾመ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ደራሲና አዘጋጅ ቅድስት ይልማን ጨምሮ ደራሲዎቹ አዜብ ወርቁና ቤዛ ሀይሉም ሀሳባቸውን እንደሚያጋሩ ታውቋል፡፡ እንደ ሳይንስ አካዳሚው ገለፃ ሌሎችም የድራማው ተሳታፊዎች የውይይቱ አካል የሚሆኑ ሲሆን የተጋበዙ የዘርፉ ምሁራንም አስተያየታቸውን ያካፍላሉ ተብሏል፡፡
በዕለቱ ከውይይቱ አስቀድሞ የተመረጡ የድራማው ክፍሎች ለእይታ የሚቀርቡ ሲሆን፣በውይይቱ  ላይ ለመታደም ለሚፈልጉ ማዕከሉ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ክፍት እንደሚሆን የማዕከሉ ሀላፊዎች ተናግረዋል፡፡

Read 13937 times