Saturday, 14 May 2022 00:00

“ከተጓዡ ማስታወሻ” እና “ከአገልጋዩ ማስታወሻ” መፅሀፎች ለንባብ በቁ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የዲያስፖራው ደራሲ ዓለማየሁ ማሞ ስራዎች የሆኑት “ከተጓዡ ማስታወሻ” እና “ከአገልጋዩ ማስታወሻ” የተሰኙ የጉዞ ማስታወሻ መፅሐፎች ለንባብ በቁ፡፡
ደረሲው እንደገለፀው ሁለቱም መፅፍት ጭብጣቸው የተለያየ ቢሆንም ደራሲው በአትላንታ ፣ዳለስ ፣ሂውስተን ፣ቦስተን፣ ኒውዮርክ፣ ጃክሰንቪል፣ ባልቲሞርና ቺካጎ ሲዘዋወር የከተባቸው ናቸው፡፡     
“ዙሪቴና ኑረቴ” ናቸው ያላቸው እነዚህ መፅሐፎች “ከተጓዡ ማስታወሻ” ዙረቴን “ከአገልጋዩ ማስታወሻ” ደግሞ ኑረቴን ይተርካሉ ሲል ደራሲው  በማስታወሻው አስፍሯል፡፡
ከአገልጋዩ ማስታወሻ የወንጌል ጉዞ ዘገባዎችን ሲይዝ ከተጓዡ ማስታወሻ ደግሞ ደራሲው በአሜሪካ ባደረጋቸው ጉብኝቶች ያያቸውን የሰማቸውን ትዝታና ተሞክሮውን ያካፈለበት እንደሆነም ታውቋል ከአገልጋዩ ማስታወሻ በ192 ገፅ ተቀንብቦ 175 ብር ለገበያ ሲቀርብ ከተጓዡ ማስታወሻ ደግሞ በ336 ገፆች ተመጥኖ  በ270 ብር ለገበያ መቅረቡ የተገለፀ ሲሆን፣ መፅሐፍቱ  በጃዕፋርና በሀሁ መፅሐፍት መደብሮች እንዲሁም በሁሉም የመፅሐፍት አዟሪዎች እጅ እንደሚገኝ ደራሲው ዓለማየሁ ማሞ ከዋሽንግተን ዲሲ መረጃ አድርሶናል፡፡
ደራሲው በ20 ዓመት የአሜሪካ ቆይታው ከ26 በላይ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 9146 times