Print this page
Saturday, 28 May 2022 13:40

“የግዮን ልጆች” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በደራሲ ታምራት ወርቁ የተሰናዳው “የግዮን ልጆች” የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በዋናነት በሀገራችን ባህል፣ ትውፊት፣ በሀገረሰባዊ ቅርሶችና የተፈጥሮ ሀብቶቻችን ዙሪያ የሚያተኩር ሲሆን በርካታ የሀገራችን ሀብቶች ለትውልድ በመከሰት ትልቅ ሚና ያለው ስለመሆኑ እውቅ ፣ምሁራን በመፅሐፉ ጀርባ ላይ ባሰፈሩት ማስታወሻ ገልጸዋል፡፡
መፅሐፉ በባህልና ሀገር በቀል እውቀቶች ዙሪያ ለመፃፍ ከተሞከሩት ስራዎች የተለየና የተደከመበት ስለመሆኑ ምሁራን የመሰከሩለት ሲሆን  በ11 ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፋፍሎና በ336 ገፅ ተቀንብቦ፣ በ280 ብርና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “የመማፀኛ ከተማ” እና “ከርቤ” የተሰኙ መፅሀፍትን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 11025 times