Saturday, 28 May 2022 14:47

ምልክቶችን እንወቅ ቀድመን እንዘጋጅ፡፡

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   በርእስነት ያነበባችሁት ምልክቶችን እንወቅ ቀድመን እንዘጋጅ የሚለው አባባል በእንግሊ ዝኛው Be prepared Before Lightning Strikes የሚል ሲሆን ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰትን የደም ግፊት ቀን ሲከበር ለቀጣዩ አመት መሪ ቃል ተደርጎ የተወሰደ ነው፡፡ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ወይም Preclampsia በየአመቱ እ.ኤ.አ ሜይ 22/ተከብሮ የሚውል ሲሆን በአለም ለአምስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ እ.ኤ.አ ሜይ 20/በኢትዮጵያ አቆጣጠር ግንቦት 12/2014 ተከብሮአል። በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት (Preeclampsia) ከዋና ዋና ከእርግዝናና ወሊድ ጋር በተያያዘ ከሚከሰቱ የእናቶች እና የጨቅላ ህጻናት ሞት ምንያቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው በበአሉ ላይ ባለሙያዎች እንደገለጹት፡፡ በየአመቱ ወደ 76.000 የሚጠጉ እናቶች እና 500.000 የሚሆኑ ህጻናት ከዚሁ ህመም ጋር በተገናኘ በአለም ላይ ህይወታቸው ያልፋል፡፡ በኢትዮጵያም በወሊድ ጊዜ ከሚከሰተው ከደም መፍ ሰስ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ የእናቶች ሞት ምክንያት ሲሆን በአንዳንድ ሆስፒታሎች ለምሳሌም…በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ቀዳሚ የእናቶች እና የህጻናት ሞት ምክንያት ነው፡፡
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት (Preeclampsia) እርጉዝ በሆነች ወይም በአራስ ሴት አካል ውስጥ ያሉ ክፍሎች ላይ እክል የሚፈጥር እና ከፍተኛ የደም ግፊት የሚያስ ከትል ህመም ነው፡፡ ይህ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ከእናቲቱ በተጨማሪም በጽንስ ላይ የተለያዩ ችግሮችን የሚያስከትል በሽታ ሲሆን በጊዜ ታውቆ ህክምና ካልተደረገ ከፍተኛ የጤና መቃወስ ከማስተሉ በተጨማሪ የእናቲቱንም ሆነ የጽንሱን ህይወት እስከማሳ ጣት ሊያደርስ ይችላል፡፡  
የእርግዝና ደም ግፊት የሚከሰተው መቼ ነው?
አብዛኛውን ጊዜ በእርግዝና 2ኛው አጋማሽ ማለትም ከሀያ ሳምንት በሁዋላ ይከሰታል፡፡ ልጅ ከተወለደ በሁዋላም ሊከሰት ይችላል፡፡
የእርግዝና ደም ግፊት መንስኤው ምንድን ነው?
በተለያየ ጊዜ ጥናቶች ቢደረጉም አንዳንድ ሴቶች ለምን በእርግዝና ወቅት የደም ግፊት እንደሚይዛቸው በትክክል አልታወቀም፡፡ ወይም የዚህን በሽታ መንስኤ ለይቶ ለማወቅ አልተቻለም። ነገር ግን ከዚህ በታች የተጠቀሱት ምክንያቶች ተጋላጭ ያደርጋቸዋል፡፡
እርግዝና የመጀመሪያቸው ከሆነ፤
ከዚህ በፊት በእርግዝና ግዜ የደም ግፊት የታየባቸው ወይም በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸው ከሆነ፤
ከዚህ በፊት የደም ግፊት ፤የኩላሊት ወይም ሁለቱም በሽታ የነበረባቸው ከሆነ፤
እድሜአቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑ፤
እርግዝናው መንታ ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን፤
እንደ ስኩዋር አይነት ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው፤
ከመጠን በላይ የሰውነት ክብደት፤
አንዲት ነፍሰ ጡር ደም ግፊት ቢኖርባት በልጇላይ ምን ሊያስከትል ይችላል?
የልጁ ክብደት ከእርግዝና ጊዜ ጋር ሲታይ የቀነሰ ይሆናል፤
የወሀ ሽንት መቀነስ፤
በእትብት በኩል ለልጁ የሚደርሰው ደም መቀነስ፤
እንዲሁም ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እንዳለ ሊሞት ይችላል፡፡
የእርግዝና ደም ግፊት ምልክቶቹ ምንድናቸው?
የበሽታው የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ምንም አይነት ምልክት አይታይም፡፡ በምርመራ ጊዜ የግፊት መጨመር ከ140/110 በላይ ከሆነ እና ሽንት ውስጥ ያለው ፕሮቲን መጨመር ይታያል፡፡ በተጨማሪም ህመሙ አደገኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ፤
ከባድ እራስ ምታት፤
የእይታ ለውጥ (የእይታ ብዥ ማለት፤ የእይታ መጋረድ)፤
ትንፋሽ ማጠር፤
በሆድ የላይኛው ክፍል ላይ ከባድ የሆነ የህመም ስሜት፤
ከፍተኛ የደም ግፊት ከ(160/110) በላይ ፤
የፊትና የእጆች ማበጥ፤
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊትን ለመከላከል ምን ይደረግ በሚለው ዙሪያ በእርግ ዝና ወቅት የሚከሰትን የደም ግፊት Preeclampsiaን በሚመለከት ፕሮጀክት እየሰሩ ያሉትን ዶ/ር ድልአየሁ በቀለን አነጋግረናል፡፡ ዶ/ር ድልአየሁ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት እና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ጽንስና ማህጸን ሕክምና የትምህርት ክፍል ኃላፊ ናቸው፡፡  
ዶ/ር ደልአየሁ እንዳሉት ብዙ ጊዜ ነብሰጡር የሆኑ ሴቶች ወደ ሕክምናው የሚቀርቡት ህመሙ ከጸና በሁዋላ እና የደም ግፊቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የማንቀጥቀጥ፤ትንፋሽ ማጠር ፤አእምሮአቸውን መሳት፤የእይታ ብዥ ማለት…ሲያጋጥማቸው በመሆኑ ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን የእርግዝና ክትትላቸውን አስቀድመው በተገቢው ቢያደርጉና ሕክምናውን አስቀድሞውኑ ቢጀምሩ እንደዚህ ካለው ደረጃ ስለማይ ደርሱ ጉዳቱን መቀነስ ይቻላል፡፡ ከእርግዝና በፊት አስቀድሞውኑ የደም ግፊት ሕመም ያለባት ሴት ከመጸነስዋ በፊት የደም ግፊቱ በጤናዋም ላይ ይሁን በጽንሱ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ችግር አስቀድማ ብታወቅ የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል። በተደጋጋሚ እንደሚነገረውም ማንኛዋም ሴት ሕመም ይኑርባ ትም አይኑርባትም ከመጸነስዋ በፊት ሐኪምዋን ብታማክር የእናቶችን እና የሕጻናቱን ሞት ለመቀነስ በጣም ይረዳል፡፡ ስለዚህ በእርግዝና ደም ግፊት የተጋለጡ እናቶችን ለመለየትና እድሉን ለመቀነስ የቅድመ ወሊድ ክትትል በመጀመሪያ ሶስት ወር መጀመር ትክክለኛ እርምጃ ይሆናልብለዋል ዶ/ር ድልአየሁ፡፡
እርጉዝ እናቶች የደም ግፊት ሊይዛቸው ከሚችሉባቸው ምክንያቶች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ የክብደት መጨመር እና የስኩዋር ሕመም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሴቶች ባጠቃላይ አስቀ ድሞውኑ የነበሩ የጤና ችግሮችንም ይሁን በእርግዝና ጊዜ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚገመ ተውን አደጋ ለመቀነስ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡  
ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የደም መፍሰስ ተከትሎ በአለም አቀፍ ደረጃ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት Preeclampsia በአለም አቀፍ ደረጃ ገዳይነቱ የተረጋገጠ የእና ቶች እና ጽንስ ወይንም ጨቅላዎቻቸው ህይወት ጠንቅ ነው። ይህንን በሽታ ለማስወ ገድና እናቶችንና ልጆችን ለማዳን ብዙ ስራ መሰራት እንዳለበት የታመነ በመሆኑ በዚህ እትም እንግዳችን ዶ/ር ድልአየሁ በቀለ ፕሮጀክት በመስራት ላይ ናቸው፡፡ እሳቸውም እን ደሚሉት በአለም አቀፍ ደረጃ በአመት እ.ኤ.አ ሜይ 22 አለም አቀፍ ከእርግዝና ጋር በተ ገናኘ የሚከሰተውን የደም ግፊት ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ማክበራችን ከዚህ ጋር ወደፊት መፍት ሔው በምን መንገድ መቀረጽ አለበት የሚለውን ለማጉላት ነው፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ህብረተሰቡ ስለ Preeclampsia በደንብ እንዲያውቅ ከማድረግ ባሻገር በህክምናው ዘርፍም ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ የሚያስችል ስራ በመስራት ላይ ነን ብለዋል ዶ/ር ድልአየሁ፡፡
እንደ ዶ/ር ድልአየሁ ማብራሪያ በአለም ላይ በየአመቱ May ወሩ ሙሉ እንዲሁም በተለ ይም እ.ኤ.አ May 22 በተለያየ መንገድ ስለ Preeclampsia እየተወራ ያልታወቀውና በቀላሉ መፍትሔ ሊደረግለት የሚገባው በሽታ በህብረተሰቡም ይሁን በሕክምና ባለሙያዎች እንዲሁም በሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን እውቅና እንዲያገኝ የማድረግ ስራው ወደፊት በሀገራችን በሁሉም አካባቢዎች እንዲከበር እና እናቶችና ህጻናቶቻቸውን እንድናድን የሚል ሀሳብ አለ፡፡
የእናቶችን ሞት ሙሉ በሙል ለመቀነስ ህብረተሰቡ ስለ Preeclampsia ንቃተ ህሊናውን ማዳበር፤የእርግዝና ክትትል አድርገው አስቀድሞ መፍትሔ እዲያገኛ፤ወይንም የህመሙን ምልክት ተረድተው ቶሎ መፍትሔ እንዲፈልጉ ከተደረገ  ህመሙ መፍትሔ ያለው ህመም ነው፡፡ በተለይም ለህመሙ ተጋላጭ ይሆናሉ ተብሎ የሚገመቱትን እናቶች አስቀድሞ ለይቶ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ አንዱ የፕሮጀክቱ አላማ ሲሆን እስከአሁን ድረስ ይህ ተግባ ራዊ የሚሆነው በትላልቅ ሆስፒታሎች ስለሆነ ይህንን በመላው የአገሪቱ አከካባቢዎች በጤና ጣቢያ ደረጃ አውርዶ ተግባራዊ ማድረግ ዋናው አላማው ነው፡፡ ወደፊት ፕሮጀክቱ ሲያልቅ የተሻለ አሰራር በመላው ሀገሪቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ይዘረጋል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል ዶ/ር ድልአየሁ በቀለ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት፡፡

Read 11613 times