Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 06 October 2012 13:55

ቴክኖ ሞባይል 20 ሞዴል ሞባይሎች እየገጣጠመ ነው

Written by 
Rate this item
(15 votes)

ደንበኞቻችን ሊጠቀሙ የሚችሉባቸውን ኢትዮጵያዊ ይዘት ያላቸው አፕሊኬሽኖች ሶፍትዌር ሰርተን፣ ለምሳሌ ባህላዊ ጨዋታ ገበጣ፣ ጉርሻ፣ የሰፈሮች ካርታ፣ ከአማርኛ ወደ ፈረንጅ፣ ከፈረንጅ ወደ አማርኛ የሚቀይር የቀን መቁጠሪያ… ሶፍትዌሮችን እየገጠምን ነው፡፡ የሁለተኛው ምዕራፍ ዕቅዶች ሲፈፀሙ ይዘጋና ሶስተኛው ምዕራፍ ወደሚጀመርበት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይ ሲ ቲ) ፓርክ እንሄዳለን፡፡ 2ኛው ምዕራፍ ዕቅዳችን 200ሺህ ሞባይሎች መገጣጠም ሲሆን ለ300 ኢትዮጵያውያንናለ 15 የውጭ ኤክስፐርቶች የሥራ ዕድል ይፈጠራል፡፡

የአገራችን የሞባይል ቴክኖሎጂ ዕድገት ፈጣን ሊባል የሚችል ነው - የቴሌ ኔትዎርክ ደካማነት ሳይዘነጋ ማለት ነው፡፡ የዛሬ 13 እና 14 ዓመት ገደማ የሞባይል ቴሌፎን ቴክኖሎጂ ሲጀመር፣ እንደዛሬው ሳይሆን በጣም ውድና ብርቅዬ ነበር፡ታስታውሱ እንደሆን ዛሬ 30 ብር የወረደው ሲም ሳርድ በጣም ውድ ነበር፡፡ የመጀመሪያውን ሲም ካርድ ዋጋ ባላስታውሰውም፤ 44 ቤት ሳወጣ፣ ከመቶ ብር የአየር ሰዓት ጋር 400 ብር ነበር፡፡ ቀፎው ደግም እንደየዓይነቱ ከ700 እስከ 1200 ብር ነበር፡፡ ኧረ ከዚያም በላይ፡፡ ለሲም ካርድ 400፣ ለርካሽ ቀፎ 700 ብር በአጠቃላይ 1100 ብር ነው ያወጣሁት፡፡

ይኼ እንግዲህ ዝቅተኛው ዋጋ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከ1500-2000 እና ከዚያም በላይ የገዙ አሉ - እንደአቅማቸው፡፡ በቅርቡ ዝቅተኛው የሞባይል ዋጋ ከ15 ብር የአየር ሰዓት ጋር 230 ብር ሲባል ሰምቻለሁ፡፡

ይኼ ታዲይ አይገርምም ትላላችሁ? ወደፊትማ ከዚህም በጣም ባነሰ ወይም ዕቃ ስንገዛ እንደምርቃት ሊሰጠን ይችላል የሚል ተስፋ አለኝ፡፡ ለምን መሰላችሁ ይህን የምለው? ድሮ ልጅ ሆነን ዘይት፣ ቡና፣ ስኳር … ለመግዛት ሱቅ ስንላክ፣ አረብ ነጋዴዎች ወይም ሌላም ባለሱቅ፣ በሌላም ጊዜ ከእነሱ እንድንገዛ ጉርሻና ማባበያ ከረሜላ ወይም ስኳር ይመርቁልን ነበር፡፡ ወደፊትስ የገበያ ፉክክርና ውድድር ሲበዛ ምርቃት አይመጣም ትላላችሁ?

የሞባይል ቴክኖሎጂ ሲጀመር በአስገራሚነቱና በአስደናቂነቱ “አጀብ ጉድ!” የተባለለት ስልክ፣ በአስርት ዓመት ገደማ አጭር ጊዜ መገጣጠም መጀመር የቴክኖሎጂው ሽግግር ዕድገት ፈጣን መሆኑን ያመለክታል፡፡ በቂ ባይባሉም በአሁኑ ወቅት በጣት የሚቆጠሩ የሞባይል መገጣጠምያ ፋብሪካዎች ሥራ ጀምረዋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ቴክኖ ሞባይል ነው፡፡ ይህ ፋብሪካ በኢትዮጵያዊና በቻይና ባለሀብቶች ሽርክና የተቋቋመ ሲሆን፣ በያዝነው ወር የተመሠረተበትን አንደኛ ዓመት አክብሯል፡፡ ስድስት ሞዴሎች በማምረት ሥራ የጀመረው ቴክኖ በአሁኑ ወቅት ሞዴሎቹን 20 አድርሶ፣ በወር 80ሺህ ሞባይሎች እያመረተ ነው፡፡ የኩባንያው ዕቅድ አሁን በያዘው 2ኛ ምዕራፍ መጨረሻ 200ሺህ ሞባይሎች፣ በ3ኛውና 4ኛው ምዕራፍ መጨረሻ 400ሺህ ሞባይሎች ማምረትና ወደ ውጭ መላክ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያዊው ሸሪክና ባለሀብት አቶ ሌቪ ግርማ ነው፡፡ አቶ ሊቪ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በጡረታ የተገለሉት የአቶ ግርማ ዋቄ ልጅ ነው፡፡ በቴክኖ ዙሪያ አቶ ሌቪ ጋር ያደረግነውን ቃለ-ምልልስ በዚህ መልኩ አቅርበዋል፡፡

የት ተወለድክ? ዕድገትና ትምህርትስ?

የተወለድኩት አዲስ አበባ ነው - በ1967 ዓ.ም፡፡ ዕድገቴ ግን በተለያዩ አገራት ነው፡፡ አባቴ የአየር መንገድ ሠራተኛ ስለነበሩ ጋና፣ ታንዛኒያ፣ ጀርመን፣ አሜሪካ፣ … ኖረናል፡፡ በኢንተርናሽናል ፋይናንስ ኤም ቢ ኤ አለኝ፡፡

ሥራ የጀመርከው ምን መ/ቤት ነው?

የኮሌጅ ትምህርቴን ስጨርስ ሥራ የጀመርኩት አሜሪካ ነው - ኤቲ ኤንድ ቲ (አሜሪካን ቴሌግራፍ ኤንድ ቴሌፎን) በተባለና በግዙፍነቱ 2ኛ በሆነው የአሜሪካ ቴልኮም ነው፡፡ በዚያ ድርጅት በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ለ8 ዓመት የሠራሁ ሲሆን፣ በ2006 ዓ.ም ከድርጅቱ ስለቅ የኤር ኤንድ ቲ ዋየርለስ ዳይሬክተር ነበርኩ፡፡ ድርጅቱ 80 ሚሊዮን ደንበኞች ያሉትና ሦስት ድርጅቶች ተጣምረው የፈጠሩት ነው፡፡

ዳይሬክተር ደረጃ ደርሰህ ለምን ለቀቅህ?

በ2006 ዓ.ም ኖኪያ ኔትዎርክስ በድርጅቱ ተቀጥሬ የታንዛንያ፣ የሲሽልስና አካባቢው ኃላፊ ሆኜ እንድሠራ ጠየቀኝ፡፡ እኔም ጥያቄውን ተቀብዬና ኤቲ ኤንድ ቲን ለቅቄ ኖኪያ ኔትዎርክን ተቀላቀልኩ፡፡ ታንዛንያ ለአንድ ዓመት እንደሠራሁ፣ ኖኪያ ኔትዎርክስና ሲመንስ ተዋህደው ኖኪያ ሲመንስ ኔትዎርክ በመባል ይጠሩ ጀመር፡፡ በዚያን ጊዜ ኖኪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮችን እንድመራ መረጠኝ፡፡

የኖኪያን የአማርኛ ሞባይል ባስመረቅንበት 2007 ዓ.ም፡፡ ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ነው በ2008  የተዋሃደውን ድርጅት ሳይሆን ኖኪያን ብቻ ወክዬ በኢትዮጵያ የተለያየ ጥናት እንዳደርግለት መደበኝ፡፡ በዚያ መሠረት እንዴት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባት እንደሚቻል፣ እንዴት ቀረጥ ማስቀነስ እንደምንችል፣ .. በአጠቃላይ በርካታ ሥራዎች ሠራሁ፡፡ በዚያን ወቅት የኢትዮጵያ ገበያ 98 በመቶ በኮንትሮባንድ የተጥለቀለቀ ነበር፡፡ የጥናቱ ዓላማ በመላው አፍሪካ ቀረጥ ከቀነሰ፣ ኮንትሮባንድም ይቀንሳል፣ ቮዳቴፎንስ፣ ሴልሮንስ … በማቅረብ የተሻለ ገቢ ይገኛል የሚል ነበር፡፡ ኮንትሮባንድ ከፍተኛ ከሆነ ደግሞ ገበያው እነሱ በሚያቀርቡት ይሞላል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ከመንግሥት ጋር ብዙ ውይይቶች አደረግን፡፡ ነገር ግን የመንግሥት አቋም እኛ ወደ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እየተሸጋገርን ስለሆነ፣ የኮምፒዩተርና የመሳሰሉትን ዕቃዎች ቀረጥ ከምንቀንስ፣ የመገጣጠሚያና የማምረቻ ኢንዱስትሪ ብትገነቡ የተሻለ ማበረታቻ ታገኛላችሁ የሚል ሆነ፡፡ እኔ ደግሞ ይህ ስትራቴጂ ይሠራል የሚል እምነት ስላልነበረኝ አልተቀበልኩትም፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን ጣና ሞባይል በ2010 ሥራ ጀመረ፣ ጥቂት ኩባንያዎችም ተከተሉት፡፡ ከዚያም መንግሥት ያቀረበውን ሐሳብ ለምንድነው ያልተቀበልኩት? ብዬ ሳጠና ትክክል እንዳልነበርኩ ተረዳሁ፡፡ የእኔ እምነት የገበያው ድርሻ ትንሽ ነው የሚል ግምት ነበር፡፡ ነገር ግን ግምቴ የተሳሳተ ነበር፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵይ ገበያ በጣም ሰፊ ነው፡፡

እንዴት ነው ታዲያ ከቴክኖ ጋር መሥራት የጀመራችሁት?

ቴክኖ በ2011 ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት ወስኖ ነበር፡፡ ስለዚህ ከኩባንያው ጋር ተገናኝቼ መነጋገር ጀመርኩና ሰፊ የገበያ ድርሻም እንደሚኖረን አረጋገጥን፡፡ ከዚያም ከበርካታ ወራት ውይይት በኋላ፣ አብረን በሽርክና ለመስራት ተስማምተን፡፡ በ2008 ያቋቋምኩትን ብራቮኮም የተባለ ኩባንያ ሸጬ፣ ሼር ገዛሁና ከቴክኖ ጋር መሥራት ጀመርኩ፡፡

ገበያው ታዲያ እንዴት ነው? እንደጠበቃችሁት አገኛችሁት?

አዎ! በኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ሞባይል ምርት እያደገ እንደሚሄድ አምነናል፡፡ ለምሳሌ ኢትዮ ቴሌኮም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የደንበኞቹን ቁጥር 40 ሚሊዮን ለማድረስ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይህ ማለት አሁን ካሉት ደንበኞች በተጨማሪ 22 ሚሊዮን ደንበኞች ገበያውን ይቀላቀላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የተለያዩ ሞዴል ሞባይሎችን፣ አክሰሰሪዎችን መገጣጠምና መለዋወጫዎች፣  በተለያዩ ቋንቋዎች ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡

ቴክኖ እንዴት ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣው?

በመንግሥት ጥያቄ ነው፡፡ መንግሥት ለማምረቻና መገጣጠሚያ ኢንዱስትሪዎች ማበረታቻና ድጋፍ ለመስጠት የገባውን ቃል ተከትሎ ነው የገባው፡፡ ሌላው ደግም ወደፊት አፍሪካ ቁጥር አንድ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚካሄድበት አህጉር መሆኗን በመገንዘብ ነው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ አፍሪካ የተለየዩ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩባት ስለሆነች በሕዝቡ ቋንቋ ሶፍትዌር በመሥራት ገበያውን ለመቆጣጠር ጭምር ነው፡፡

ቴክኖ መሠረቱን ያደረገው የት ነው? በአፍሪካ ሌላ የሚሠራበት አገር አለ?

ዋና መ/ቤቱ ሆንግኮንግ ነው፡፡ በ18 የአፍሪካ አገራትም ጠንካራ የገበያ ሽፋን አለው፡፡ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ፣ … ብዙ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ ሰፊና በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ ስላላት ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች የበለጠ ተስፋ ሰጪ ገበያ ያላት አገር ናት፡፡

አሁን ምን ምንድነው የምታመርቱት?

ወደ ዝርዝሩ ከመሄዳችን በፊት የአሠራር ዕቅዳችንን ልግለጽ፡፡ እኛ ሥራችንን ለማከናወን የተነሳነው በአራት ምዕራፎች ነው፡፡ በአንደኛው ምዕራፍ ሞባይሎችን መገጣጠም ሲሆን በዚህን ጊዜ ውስጥ 60ሺህ ሞባይሎችን መገጣጠም ነው፡፡ ይህ ምዕራፍ ተከናውኖ አልቆ ተዘግቷል፡፡

አሁን ሁለተኛውን ምዕራፍ ጀምረናል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚሠራው ሞባይሎችን መለዋወጫና አክሰሰሪዎችን መገጣጠም፣ የአገር ውስጥ ቋንቋዎች ሶፍትዌር በሞባይሎች መጫን፣ አገር አቀፍ የጥገና ማዕከል መክፈት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት በ6 ሞዴሎች ጀምረን አሁን 2 ሞዴሎች እያመረትን ነው፡፡ በአማርኛ፣ ኦሮሚፋ፣ ትግርኛና በእንግሊዝኛ የሚሠሩ ሞባይሎች እየገጣጠምን ነው፡፡ ለሞባይሎቹ መለዋወጫና አክሰሰሪዎች መገጣጠም ጀምረናል፡፡ ለምሳሌ ኦሪዲናል የቴክኖ ባትሪ፤ ስክሪን፣ የጆሮ ማዳመጫ፣ ቻርጀር እንዲሁም በአስር ትላልቅ ከተሞች፣ ባህርዳር፣ መቀሌ፣ ድሬዳዋ አዳማ፣ ጂማ፣ ሀዋሳ፣ ጐንደር፣ ደሴ፣ በመርካቶና በፒያሳ የጥገና ማዕከላት እንከፍታለን፡፡

በፒያሳ ሃሮን ሕንፃ የተከፈተው ትልቅ የጥገና ማዕከል ሥራ ጀምሯል፡፡ በሌሎች ቦታዎችም በቅርቡ እንጀምራለን፡፡ እነዚህ ማዕከላት ከታህሳስ በፊት ይከፈታሉ፡፡

ደንበኞቻችን ሊጠቀሙ የሚችሉባቸውን ኢትዮጵያዊ ይዘት ያላቸው አፕሊኬሽኖች ሶፍትዌር ሰርተን፣ ለምሳሌ ባህላዊ ጨዋታ ገበጣ፣ ጉርሻ፣ የሰፈሮች ካርታ፣ ከአማርኛ ወደ ፈረንጅ፣ ከፈረንጅ ወደ አማርኛ የሚቀይር የቀን መቁጠሪያ… ሶፍትዌሮችን እየገጠምን ነው፡፡ የሁለተኛው ምዕራፍ ዕቅዶች ሲፈፀሙ ይዘጋና ሶስተኛው ምዕራፍ ወደሚጀመርበት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይ ሲ ቲ) ፓርክ እንሄዳለን፡፡ 2ኛው ምዕራፍ ዕቅዳችን 200ሺህ ሞባይሎች መገጣጠም ሲሆን ለ300 ኢትዮጵያውያንናለ 15 የውጭ ኤክስፐርቶች የሥራ ዕድል ይፈጠራል፡፡

በአይ ሲቲ ፓርክ 19,232 ካ.ሜ ቦታ ጠይቀናል፡፡ በዚያ ስፍራ ሞባይል መገጣጠም ሳይሆን ራሳችን ሞባይሎችን፣ መለዋወጫዎችና አክሰሰሪዎች መምረት ሌሎች ተጨማሪ ባህላዊና አገር በቀል አፕሊኬሽኖች በሞባይሎቻችን እንጭናለን፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ የጥገና ማዕከላትን እንከፍታለን፡፡ የዚህ ምዕራፍ የሞባይል ምርት ዕቅዳችን 400 ሺህ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ትልቅ ሞባይል ማምረቻ ፋብሪካ ይኖረናል፡፡ የሠራተኛው ቁጥር 600 የአገር ውስጥና 15 የውጭ ኤክስፐርቶች ይኖራሉ፡፡

የ4ኛው ምዕራፍ ተግባራት ከ3ኛው ምዕራፍ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ልዩነቱ አንድ ብቻ ነው፡፡ እሱም ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚደረግ ኤክስፖርት ነው፡፡ አሁን በጀመርነው 2ኛው ምዕራፍ መጨረሻ ለሙከራ ኤክስፖርት ለመጀመር አቅደናል፡፡

የሞባይላችሁ ጥራት እንዴት ነው?

እኛ ለጥራት ከፍተኛ ትኩረት እንሰጣለን፡፡ የምንገጣጥማቸው ሞባይሎች ጥራት በሶስት ደረጃ የተከፈለ ነው፡፡ የመጀመሪያው ዕቃው ከውጭ ሲገባ ብልሽት የሌለው መሆኑ ይረጋገጣል፡፡ ሁለተኛ ከተገጣጠመ በኋላም ይታያል፡፡ ሶስተኛ ታሽጎ ለገበያ ከመቅረቡ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ይመረመራል፡፡ከዚህም በተጨማሪ ለምንሸጣቸው ሞባይሎች የአንድ ዓመት ከአንድ ወር (13 ወር) ዋስትና እንሰጣለን፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ሞባይሉ ቢበላሽና ብልሽቱ በተጠቃሚው የተፈጠረ ሳይሆን ከፋብሪካው ሥራ ጋር የተያያዘ ከሆነ በነፃ እናድሳለን፡፡ ብልሽቱ የተጠቃሚው ከሆነ ደግሞ በክፍያ እንጠግናለን፡፡ ለምሳሌ ሞባይሉ በደንብ የማያሰማ ከሆነ ብልሽቱ የፋብሪካው ስለሆነ በነፃ ይታደሳል፡፡ ውሃ ገብቶበት ከተበላሸ ደግሞ በእኛ የተፈጠረ ችግር ስላልሆነ በክፍያ እናድሳለን፡፡

በአሁኑ ወቅት ሌሎች መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች ሥራ እየጀመሩ ስለሆነ ዋጋ ሊቀንስና ውድድር ሊኖር ይችላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ትርፋማ እንሆናለን ትላላችሁ?

በሞባይል ኢንዱስትሪ ትልቁ ችግርና ስጋት ኮንትሮባንድ ነው፡፡ ታክስ ተከፍሎ ሲገባ ታክሲ ሁሉንም ነገሮች ጨምሮ 38 በመቶ ነው፡፡ ኮንትሮባንድ ባይቀረጥም ወጪ አለው፡፡ ነገር ግን 38 በመቶ አይሆንም፡፡ ተጠቃሚው በኮንትሮባንድ የገባ ሞባይል ከእኛ አነስ ባለ ዋጋ ሊያገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከእኛ ሲገዛ ተጨማሪ ጥቅም ይገኛል፡፡ እኛ ዋስትና እንሰጣለን፤ ከኦሪጅናል ባትሪ… ከኦሪጅናል ቻርጀር… ጋር እናቀርብለታለን፡፡ስለዚህ ተጠቃሚው ከኮንትሮባንድ ነጋዴዎች አነስ ባለ ዋጋ ቢገዛም የሚያገኘው ተጨማሪ ጥቅም ትንሽ ነው ወይም አይኖረውም፡፡ ቢበላሽበት ዋስትና የለውም፡፡ የሸጠለትን ነጋዴ ለውጥልኝ ቢለው “እኔ አልሰራሁትም፤ እንደመጣ ነው የሸጥኩልህ” ነው የሚለው ስለዚህ ተጠቃሚው ተጨማሪ ጥቅሞችና ነገ ቢበላሽ ዋስትና የሌለውን ሞባይል በቅናሽ ዋጋ ስላገኘ አይገዛም፡፡ ዋጋው ቢጨምርም ተጨማሪ እሴትና ዋስትና ያለውን ነው የሚገዛው፡፡ ይህን በተግባርም አይተናል፡፡ ስለዚህ የአገር ውስጥ ምርት በጨመረ ቁጥር ኮንትሮባንድ ጭራሹን ባይጠፋም እየቀነሰ ይሄዳል፡፡

 

 

 

 

p style=

Read 13844 times Last modified on Saturday, 06 October 2012 15:47