ዋጋው ከአንድ የአሜሪካ አዲስ መኪና መሸጫ በ307,000% ይበልጣል
ታዋቂው የጀርመን የመኪና አምራች ኩባንያ መርሴድስ እ.ኤ.አ በ1955 የተመረተችዋንና መርሴድስ-ቤንስ ኤስኤልአር የተባለችዋን ጥንታዊ እጅግ ውድ መኪና ክብረ ወሰን ባስመዘገበ ሽያጭ በ143 ሚሊዮን ዶላር መሸጡን አስታውቋል፡፡
ኩባንያው ለረጅም አመታት በልዩ ቅርስነት አስቀምጧት የኖረችዋን ይህቺን ውድ መኪና በቅርቡ ጀርመን ውስጥ ማንነቱ ላልታወቀ አንድ ግለሰብ በ142 ሚሊዮን ዶላር መሸጡን እንዳስታወቀ የዘገበው ሲኤንኤን፤ ይህም በአለማችን የመኪኖች ሽያጭ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡንና መኪናዋ የተሸጠችበት ዋጋ ከአንድ የአሜሪካ አዲስ መኪና አማካይ የመሸጫ ዋጋ በ307,000% ብልጫ እንዳለው መነገሩንም አመልክቷል፡፡
በታዋቂው አጫራች ኩባንያ ሱዝቤይ በኩል ከተከናወነው ሽያጭ የተገኘው ገንዘብ የሜርሴድስ-ቤንዝ ፈንድ የተባለውንና ነጻ አለማቀፍ የትምህርት ዕድል የሚሰጠውን በጎ አድራጊ ተቋም ለማቋቋም እንደሚውል የጠቆመው ዘገባው፤ ከዚህ በፊት በአለማችን በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠች መኪና ተብላ የተመዘገበችው በ1963 የተመረተችዋና በ2018 ላይ በ70 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠችው ፌራሪ 250 ጂቲኦ መኪና እንደነበረችም ዘገባው አስታውሷል፡፡
Published in
ከአለም ዙሪያ