Saturday, 04 June 2022 18:17

መቶ ኪሎ የገብስ ዱቄት የፈጀው ገንፎ አድናቆትን አትርፏል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ጭላሎ ሚድያና ማስታወቂያ ድርጅት ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀው ዓመታዊ የአርሲ ገበሬዎች ፌስቲቫል ላይ የቀረበው በትልቅነቱ የመጀመሪያው ነው የተባለው ገንፎ አድናቆትን አትርፏል፡፡ በአርሲ በቆጂ ሁለተኛው ዓመት የገበሬዎች ፊስቲቫል ባለፈው እሁድ ግንቦት 14 ቀን 2014 ዓ.ም በበቆጂ የአትሌቶች ማሰልጠኛ ሜዳ በድምቀት ተካሂዷል።
 በእለቱ በርካታ አርሶ አደሮችና ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ለእይታ ያቀረቡ ሲሆን የተፈጥሮ ማዳበሪያዎች፣ የቢራ ገብስ ምርጥ ዘር፣ የተባይ ማጥፊያ፣ የአገር በቀል እፅዋት ዘሮች፣ ባህላዊ የእርሻ መሳሪያዎችና በርካታ ከግብርና ጋር የተያያዙ ግብዓቶች ለተመልካች ቀርበዋል።
በፌስቲቫሉ ላይ የፈረስ ጉግስ፣ ሙዚቃና የትራክተር ትርዒት የቀረበ ሲሆን ከሁሉም በላይ አድናቆትን ያተረፈው ግን በፌስቲቫሉ አዘጋጅ ጭላሎ ሚድያና ማስታወቂያ ድርጅት መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ፣ ጋዜጠኛና የመድረክ መሪ አንዷለም ጌታቸው ሀሳብ አፍላቂነት የተዘጋጀው በትልቅነቱ የመጀመሪያው ነው የተባለው ገንፎ ነው። ገንፎው መቶ ኪሎ የገብስ ዱቄት መፍጀቱ ታውቋል፡፡



Read 1689 times