Saturday, 04 June 2022 18:32

ሳዑዲ አረቢያ የአለማችንን እጅግ ግዙፍ ህንጻዎች እየገነባች ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ500 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሙሉ ለሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተንቆጠቆጠች አዲስ ከተማ በመገንባት ላይ የምትገኘው ሳዑዲ አረቢያ፤ በከተማዋ የምትሰራቸው መንትያ ህንጻዎች በግዝፈታቸው አዲስ የአለም ክብረ ወሰን እንደሚያስመዘግቡ አስታውቃለች፡፡
ኒኦም የሚል ስያሜ በተሰጣትና በግንባታ ላይ በምትገኘው አዲሷ የሳዑዲ አረቢያ ግዙፍ ከተማ የሚገነቡት እነዚህ መንትያ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ከ500 ሜትር በላይ ቁመት እንደሚኖራቸውና ወደ ጎንም በአስርት ማይሎች ስፋት እንደሚኖራቸው የዘገበው ብሉምበርግ፤ ከቀይ ባህር ዳርቻ አካባቢ የሚሰሩት ህንጻዎች ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለቢሮ አገልግሎት እንደሚውሉ መነገሩን አስነብቧል፡፡
በአለማችን አራተኛው ሰማይ ጠቀስ ህንጻ የሆነውና 601 ሜትር ቁመት ያለው አብራጅ አልቤት ህንጻ መገኛ የሆነችው ሳዑዲ አረቢያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተሟላችዋንና ለአለማቀፍ ቱሪስቶች መናኸሪያ እንድትሆን ያሰበቻትን ኒኦም ከተማ ለመገንባት ማቀዷን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገችው በ2017 ጥቅምት ወር ላይ እንደነበርም ዘገባው አስታውሷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአለማችን እጅግ ረጅሙ ህንጻ በዱባይ የሚገኘውና 828 ሜትር ቁመት ያለው ቡርጂ ከሊፋ መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፣ ሳዑዲ አረቢያ በ2013 ላይም ሌላ ከዚህ ህንጻ የሚረዝም ጂዳ ታወር የተባለ ህንጻ መገንባት መጀመሯን ጨምሮ አስታውሷል፡፡

Read 3122 times