Tuesday, 07 June 2022 00:00

ኤምቲኤን እና ናይኪ በአፍሪካ እጅግ ተወዳጅ ብራንዶች ተብለዋል

Written by 
Rate this item
(5 votes)

ናይኪ ለ5ኛ አመት በአፍሪካውያን የሚወደድ አፍሪካዊ ያልሆነ ብራንድ ተብሏል

            በቴሌኮም ዘርፍ የተሰማራው ኤምቲኤን ብራንድ አፍሪካ የተባለው ተቋም ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው የ2022 የፈረንጆች አመት በአፍሪካ እጅግ ተወዳጅ የሆኑ የንግድ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ ከአፍሪካ ኩባንያዎች የ1ኛ ደረጃን መያዙ ተነግሯል፡፡
የናይጀሪያው ዳንጎቴ በበኩሉ ተቋሙ ለ12ኛ ጊዜ ባለፈው ረቡዕ በናይጀሪያዋ ሌጎስ በተከናወነ ስነስርዓት ይፋ ባደረገው አመታዊ ሪፖርቱ፣ የአመቱ ምርጥ 100 በአፍሪካ እጅግ ተወዳጅ ብራንዶች ዝርዝር ውስጥ በምርጥ ተወዳጅ የአፍሪካ ኩራት ኩባንያ ዘርፍ የ1ኛ ደረጃን ሲያገኝ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኤምቲኤን ይከተላሉ፡፡
በአፍሪካ እጅግ ተወዳጅ አፍሪካዊ ያልሆነ ኩባንያ ዘርፍ ላለፉት ተከታታይ አራት አመታት ቀዳሚነቱን ይዞ የዘለቀው ናይኪ ዘንድሮም በተወዳጅነቱ ቀዳሚው ሲሆን፣ አዲዳስ እና ሳምሰንግ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
በአፍሪካ ተወዳጅ ከሆኑ 100 ብራንዶች መካከል 83 ያህሉ አፍሪካዊ ያልሆኑ ኩባንያዎች መሆናቸውንም የተቋሙ ሪፖርት ያሳያል፡፡ በእጅጉ ተወዳጅ አፍሪካዊ ሚዲያ ዘርፍ ደግሞ ዲኤስቲቪ እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም አንደኛ ደረጃን ሲይዝ፣ ቢቢሲ እና ሲኤንኤን ይከተሉታል፡፡ በፋይናንስ አገልግሎቶች ዘርፍ ደግሞ፣ ጂቲ ባንክ፣ ኢኮ ባንክ እና ኢኩቲ ባንክ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡


Read 19085 times