አለቀሰ ብዕር---
በዱልዱም ቢቀርጹት
ብዕር አለቀሰ
ጥቁር ቀለም ሳይሆን
ደም እያፈሰሰ---
ያላሰበው ቢጻፍ---
ያሰበው ተውጦ
እውነት ስትጨነግፍ---
እብለት ሲታይ በልጦ
ውሸት ነፍስ ዘርቶ---
ደምቆ--ገዝፎ--ጎልቶ--
ሲባባሉ አበጀህ በእምባው ሲጠቀሙ---
ቅጥፈት ሲሆን ቤቱ
ህጉ መገጥገጡ መላ መጀምጀሙ---
ቢሰለቸው ጊዜ አታካች ስብከቱ
ጥቁር ቀለም ሳይሆን
ደም እያፈሰሰ---
ብዕር አለቀሰ፡፡
መቅደስ ጀምበሩ
Published in
የግጥም ጥግ