Saturday, 11 June 2022 18:09

የትግራይ ክልል 5 ጋዜጠኞች ታሰሩ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ አምስት ጋዜጠኞች “ከጠላት ጋር ተባብራችኋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ፡፡
የታሰሩት ጋዜጠኞች ተሾመ ጠመሃሉ፣ ምስግና ስዩም፣ ዳዊት እንዲሁም መኮንን  ሃበን ሃለፎዎ፣ሃይለ ሚካኤል ገሠሠ ሲሆኑ  “ከጠላት ጋር ተባራችኋል” በሚል ነው ከሰሞኑን ለአስር የተዳረጉት ሲል የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል፡፡
ከታሰሩት ጋዜጠኖች መካከል ጋዜጠኛ ሃበን ሃለፎም ለሁለት ሳምንት ፍ/ቤት ሳይቀርብ በእስር ላይ መቆየቱን  የዘገበው ቪኦኤ፤ ጋዜጠኞቹ ለጤንነታቸው አስጊ በሆነ አኳሀን ንፅህናቸው ባልጠበቀ አስር ቤቶች መታሰራቸውን ጠቁሟል፡፡
ጋዜጠኞቹ በዋናነት የፌደራል መንግስት ትግራይን  ተቆጣጥሮ በነበረ ወቅት “ከጠላት ጋር ተባብራችኋል” ተብለው እንደተወነጀሉና ለእስር እንደተዳረጉ ነው የተሰማው፡፡
በጉዳዩ ፤ላይ  መግለጫ የሰጠው የክልሉ አቃቢ ህግ ቢሮ በበኩሉ፤ ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከሙያቸው ጋር በተያዘ ሳይሆን በፈጸሙት ወንጀል ተጠርጥረው ነው”ብሏል፡፡ “እነሱ ብቻ ሳይሆኑ በቴሌቪዥን ጣቢያው ይሰሩ የነበሩ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በወንጀል ተጠርጥረው  ታስረዋል” ሲልም ቢሮው አክሏል፡፡
ጋዜጠኞቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ዘገባው አመልክቷል፡፡



Read 1046 times