Print this page
Saturday, 11 June 2022 18:38

በአፍህ የምታመጣው ዕዳ፣ በእግርህ የምትሄደው ሜዳ፤ ይጎዳሃል! ብትናገር ያምናውን፣ ብትፈትል አንድ ልቃቂት

Written by 
Rate this item
(3 votes)

 ከዕለታ አንድ ቀን አንድ በጣም ዝነኛ የንጉስ አጫዋች በአንድ ትንሽ መንደር ይኖር ነበር፡፡ ይሄ አጫዋች፤ ንጉሹን ያዝናናል የሚለውን ማናቸውንም ቀልድ ካቀረበና ካዝናናቸው በኋላ በንጉሡ ዙሪያ ላሉት ልዩ አስተያየት ስለሚደረግላቸው ሰዎች ጥያቄ ያቀረበለት፡፡ ንጉስ እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፡-
ምረጥ ላይ ናት፡፡ እሷ ከልቧ የምትወደው አንድ ወጣት አለ፡፡ ለምርጫ የቀረቡት ግን ሶስት ወንዶች ናቸው፡፡  እነዚህን ሶስት ወጣቶች የሚፈትን ጥሩ ጥያቄ ጠይቃትና እሷ ደግሞ ሶስቱንም ትጠይቃቸዋለች፡፡ ያወቀ ያገባታል፣መንግስቴንም ይወርሳል” አሉት፡፡
“እሺ ንጉስ ሆይ! “እስከዛሬ እኔና፣ መሳፍንትና መኳንንቶቼን በአጫዋችነት ላይ የሚያዝናናው ሰው፣ ስሙ ማነው” ብለው ይጠይቋትና ትፈትናቸው” አላቸው፡፡
አጫዋቹ እንዳለው ንጉስ ለልጃቸው ይሄንኑ ጥያቄ አቀረቡላት፡፡ እሷም በበኩሏ የታዘዘችውን አደረገች፡፡ ሆኖም ልጅቷ የወደደችውን ወጣት ለማግኘት ቆርታ ተነስታለችና አማካሪዎቿን ጠርታ፤
“ይሄንን የንጉሡን አጫዋች የገባበት ገብታችሁ ተከታተሉት፡፡ የሚኖርበትን አካባቢና የሚኖሩትን ሰዎች በሙሉ አጠያይቃችሁ ስሙን ይዛችሁልኝ ኑ” ስትል አዘዘች፡፡
በአጫዋቹ ሰፈር ያሉ ሰዎች ሁሉ ተጠየቁ፡፡ የሚያውቅ ሰው ጠፋ፡፡ የማታ ማታ ግን “እኔ ስሙን ላገኝ እችላለሁ” የሚል ብልህ ሰው ተገኘ፡፡
“ውለታህን በጠየቅኸው መጠን እከፍላለሁ፡፡
ብቻ ስሙን አምጣልኝ” አለችው፡፡
“ታዛዥ ነኝ ልዕልት ሆይ! በሁለት ቀን ውስጥ እመጣለሁ” ሲል ቃል ገባ፡፡
ብልሁ ሰው፤ ያ አጫዎች ከመኖሪያ ቤቱ አጠገብ ካለች ትንሽ ጎጆ ቤት ውስጥ እሳት እያነደዱ በዙሪያው እየዞረ እንደሚጨፍር፣ የሆነ ዘፈን እንደሚዘፍንም ያውቃል፡፡ ወደዚያ ጎጆ ተከትሎት ሄደና የሚለውን ያደምጥ ጀመር፡፡
ዕውነትም አጫዋች በእሳቱ ዙሪያ እየዞረ ይጨፍራል፡፡ እንዲህ እያለም ይዘፍናል።
“ስሜ ደረባ- ደረብራባ! ልጅቷ አታውቅ!
ስሜ ደረባ-ደረብራባ! ልጅቷ አታውቅ!”
ልዕልቲቱ በዚህ መንገድ የአጫቹን ስም አወቀች፡፡ የምትፈልገውንም ሰው አገባች ይባላል፡፡
***
ንጉስ ያለ አጫዋች፣ ያለአማካሪ አይኖርም፡፡ እንደአማካሪዎቹ ብልሀትና ጥንካሬም የመንግስቱ ጥናት ይወስናል፡፡ መካር የሚያሳስተውም ንጉስ አለ፡፡ የመንግስቱን ውሎ አድሮ መፈረካከስ የሚያሳይ ነው፡፡
“መካር የሌለው ንጉሥ፣ ያለ አንድ ዓመት አይደነግስ” የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ በደራሲ ሐዲስ ዓለማየሁ “ፍቅር እስከ መቃብር” መፅሐፍ ውስጥ የምናገኛቸው ቀኛዝማች አካሉ፤ ከአሜሪካ መንግስት አማካሪ ከኪሲንጀር የማይተናሱ ናቸው! ያም ሆኖ በሼክስፒር ኦቴሎ ውስጥ የምናገኘው እኩይ-አማካሪም አማካሪ ነው። ለጥፋት የሚዳርግ አማካሪም አለና መንግስት አስተዋይ የንስር ዐይን ሊኖረው ይገባል!
ሌላው ልንገነዘበው የሚገባ ነገር አገር ብልህ ብቻ ሳይሆን፤ ልባም፣ ልባም ጀግና፣ ህዝብ የሚወደው የጎበዝ -አለቃ እንደምታፈራ ነው፡፡ የህዝብ ፍቅር አያልቅምና የሚፈጠረው ጀግና ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ጀግኖቻችንን አናክብር  እንንከባከብ!
በተለይ እንደአገራችን  ጦርነት በማይለያትና በማያበራባት አገር ጀግና መወለዱ አይቀሬና አሌ አይሉት ሐቅ ነው፡፡ “ማን ያርዳ የቀበረ፣ ማን ይመስክር የነበረ” የምንለው ከዚህ የተነሳ ነው ታሪክን እንዘክር፡፡ አበው” ማዘዝ ቁልቁለት ነው ይላሉ” ተማሪ ይታዘዛል፡፡ ተማሪ ህዝብ ይታዘዛል፡፡ ወታደር ይታዘዛል፡፡ የበታች አካል ይታዘዛል፡፡ ይህ ሁሉ በርዕቱና በሰናይ መንገድ የሚከናወን መልካም መሪና መልካም አመራር መሪዎች ነበሩ፡፡ መሪዎች አገርን ወዳፈተታቸው መውሰድ ፖለቲካዊ ተፈጥሮአቸው ነው፡፡ የማህል አገሩ ህዝብ አመፅ ሲያስቸግራቸው ነው፡፡ የማህል አገሩ ህዝብ አመፅ ሲያስቸገራቸው ከጎረቤት ጋር ግጭት ፈጥረው የትግሉን አቅጣጫ ማስቀየሳቸው diverision መፍጠር እንዲሉ ታሪክ ያሳየን ዕውነት ነው!  ዞሮ ዞሮ ግን “ሁለት አህዮች ሲራገጡ የሚጎዳው ሣሩ ነው! መንግስታት ጦር ሲሰብቁ፤ ድርጅቶችና ፓርቲዎች ሊፋጉ የሚጎዳው ህዝቡ ነው፡፡ ትግራይን፣ የጎጃም፣ የጎንደር፣ ወሎን፣ ሰሜን ሸዋን አፋርን ሱማን ያዩዋል!
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ መሪዎች ምንም ችግር እንዳልተፈጠረ ወይም ተቃራኒ የሚናገሩ ከሆነ፣ “በአፍህ የምታወጣው ዕዳ፣ በእግርህ የምትሄደው ሜዳ   ይጎዳሃል አሊያም ብትናር ደመናውን ብትፈልግ ብትፈትል አንድ ልቃቂት እንደተባለው ተረት ይሆናል፡፡

Read 12230 times
Administrator

Latest from Administrator