Saturday, 11 June 2022 18:31

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 የአብደላ እዝራ እናት "ሚርያም"፤ የስማቸው ነገር


           አበራ ለማ፣ እኔ፣ አለማየሁ ገላጋይና ጥቂት ሌሎች ሆነን፣ ከእዝራ አብደላ አክስት መኖርያ ቤት ተሰባሰበን ቆመናል።
እዝራ ያረፈ እለት።
አበራ ለማ (ደራሲ) መጠነኛ የህይወት ታሪኩን እንድፅፍና ለቀብር ሰዓት እንዳዘጋጅ ነገረኝና መጻፍ ጀመርኩ፡፡ ከአለማየሁ (ደራሲ) ጋር ሆኜ የተወሰኑትን አደራጀሁ፡፡ የእዝራን ሙሉ ስም ከስራ መታወቂያው ላይ ወሰድኩ (EZra Abdela Muhammed Sallah)፡፡ ከአባቱ ከአቶ እገሌ የሚለውን ደምብ ከዚያ ላይ ሞላሁ። ከእናቱ የሚለው ላይ ግን ችግር ተፈጠረ ፡፡
የአርባ ሁለት ዓመት ጓደኛዬ ነበር የሚለውን አበራ ለማን፣ የአብደላ እዝራ እናት ስምን ጠየቅሁ፡፡ የእናቱን ስም ማወቅ አልቻለም።  አለማየሁ ገላጋይን ወደ ጆሮው ቀርቤ ጠየቅሁ። "አንዴ በጨዋታ መሃል የነገረኝ ይመሥለኛል፤ ግን እርግጠኛ አይደለሁም" አለኝ።
 መገረሜ ከፍ እያለ መጣ!
ልጁ ማህሌትን አስጠራሁና ጠየቅዃት።
እርሷ ራሱ የአያቷን ስም ለመጀመርያ ጊዜ ለማወቅ ለማሰብ ሞከረች። ሞከረችእንጂ ለማወቅ አልቻለችም፡፡
"ቆይ መጣሁ"  ብላኝ ወደ ውስጥ  ገባችና፣ ከአንዲት ምድር ላይ ረፈድ ካደረገች ሴት ጋር ተመልሳ መጣች፡፡ "የእዝራ አክስት ናት፤ እርሷን ጠይቃት" ብላኝ እየተፋጠነች ወደ ውስጥ ነጎደች።
የእዝራን አክስት፣ የእዝራ እናት ስም ማን እንደሚባሉ ጥያቄ አቀረብኩ፡፡ ቢያንስ አሁን እርግጠኛ ነበርኩ።
ያሳዝናል፤ የተነገረኝ መልስ ‘’ኤፍሬም፤ እዝራኮ ስነ ፅሁፍ ላይ እንደምታውቀው አይነት ሰው ብቻ አይደለም፤ እጅጉን ሲበዛ ምስጢረኛ ነው፤ በጣም Reserved"
በውስጤ ይህን የእዝራን ህቡዓዊነት የአርባ ሁለት ዓመት ባልንጀራዬ ነው የሚለው አበራን ጨምሮ "እዝራኮ ከኢህአፓ  ሽንፈት በኋላ ራሱን ያገለለና ምስጢራዊ የሆነ፣ ወደ ራሱ ብቻ የተከተተ  ሰው ነው" ማወቅ ይቸግራል ሲለኝ፣ ከእናቱ ስም ጋር ምን ሊያገናኘው ይችላል በማለት፣ የእነርሱ ዝምድናና ቀረቤታ ላይ እስኪያመኝ ድረስ ጥያቄ ላይ በመውደቅ፣ ለእዝራ እናት እኔው ራሴ ‘’ሚርያም’’ የሚል ስም አወጣሁላቸውና፣ "ከእናቱ ከወይዘሮ ሚርያም፣ በመርካቶ አካባቢ ተወለደ" በማለት የጎደለውን ታሪክ ሞልቼ  በቀብሩ ሰአት ተነበበ።
እኔ ያነበብኳት የህይወት ታሪክ ወረቀት Reporter  አዲስ አድማስ፣ ኢቲቪ  መዝናኛ  ጌጡ ተመስገን ሣይቀር በነጎድጓድ ድምፁ የተረከው "ከአባቱ አብደላ ሙሃመድ ሳላህ፣ ከእናቱ ሚርያም መርካቶ አካባቢ ተወለደ" ትል የነበረችው ነች።
ሚርያም በዐረብኛ ማርያም እንደ ማለት ስለሆነ፣ ስሙም የኢስላም የክርስትና ቅይጥ በመሆኑ ነው  ሚርያም የሚል ስም ማውጣቴ።
መቼም ለዕዝራ አብደላ ማርያምን (ሚርያምን) የፀጋ እናት አድርጌ ለጊዜውም ቢሆን መሰየሜን እንደ ክብር ስቆጥረው እኖራለሁ።
ስለ ወዳጆቹም እንዲሁ በማሰብ
______________________________________________________

                          የጃዋር መሐመድ የግጭቶች ትንተና
                              ጌታሁን ሔራሞ
ጃዋር መሐመድ እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ - BBC News አማርኛ


            በቅርቡ አቶ ጀዋር መሐመድ በኡቡንቱ ሚዲያ የተደረገለትን ቃለመጠይቅ ከአንዴም ሁለቴ ተከታትዬአለሁ። ጀዋር በቃለመጠይቁ በወቅታዊ ሁኔታ መነሻነት በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ማተኮሩን ወድጄለታለሁ። በተቀረፀው ምስል ባክግራውንድ ባለው የዕይታ ሜዳ (Visual field)  የሀገሪቱ ባንዲራ “ጋቢናውን” መቆጣጠሩ፣ ይህንኑ ሀገራዊ ትኩረት የሚጠቁም ነው። የማብራሪያውም ድምፀትና ይዘት፣ የአንድ ፓርቲ አመራር ሳይሆን የሀገር መሪ ዓይነት ነበር።
በአቶ ጀዋር የኢትዮጵያ ግጭቶች ሰበብና ውጤት ትንተና (Cause-Effect Analysis & Conflict Mapping) ላይ ወደ ፊት የማነሳቸው ጥያቄዎቹ ቢኖሩኝም፣ በቃለመጠይቁ እንደተከታተልነው ከሆነ ለሀገር ሰላም ያለው ቁርጠኝነቱ ይበል የሚያሰኝ ነው። እንዲሁም የዘመናችን ሲቪል ጦርነቶች ቅርፅና ይዘት ከቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ከተካሄዱት ጋር ሲነፃፀሩ መሳ ለመሳ መሆናቸውን አስመልክቶ ሊቢያን፣ ሶሪያንና የመንን በዋቢነት በመጥቀስ  የሰጠው ትንታኔም ምርጥ የሚባል ነው። በእርግጥ እኔም ከ8 ወራት በፊት በሶስት ልጥፎቼ  በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ ላይ መፃፌ ይታወሳል።  ግጥምጥሞሹ ቢገርመኝ የእሱን የኡቡንቱ ሚዲያ ገለፃውንና የኔን ፅሁፎች ዳግም ላካፍላችሁ ወደድኩ። ድግግሞሽ አፅንዖት መስጫና ግንዛቤን መፍጠሪያ አንዱም መንገድ ነው፤ ቀደም ሲል ፅሁፎቼን ላላነበቡ ደግሞ አጋጣሚው ጥሩ ነው፤ እናም በትዕግስት አንብቡት ለማለት ያህል ነው ...
አቶ ጀዋር በቃለመጠይቁ  ከ1:29 - 1-37 ባለው ጊዜ ያካፈለው አንኳር መልዕክት ቃል በቃል ይህን ይመስላል።
“እንግዲህ እስር ቤት እያለሁ ብዙ አንብቤ ነበርና አንዱ የተረዳሁት ነገር፣ የዱሮ የእርስ በእርስ ጦርነቶችና የአሁን የእርስ በርስ ጦርነቶች ውጤታቸው የተለያያ ነው። ምክንያቱም በድሮ የእርስ በእርስ ጦርነቶች probably pre 200 pre 1991 የነበሩ እርስ በእርስ ጦርነቶች የተሳታፊው መጠን ውስን ነበር። በአንድ ሀገር አንድ መንግስትና may be አንድ ሁለት አማፂ ነበር የሚዋጋው። እንደዚህ ዓይነት ግጭቶች ቢረዝሙም በአንድ ወገን አሸናፊነት ሲጠናቀቁ  አዲስ መንግስት ይመሠረታል። ሀገር ይቀጥላል። የሀገር ውስጥ ተሳታፊዎች ወይም domestic actors የምንላቸው domestic entrepreneurs የምንላቸው ውስን ናቸው። እንደዚሁም ደግሞ exrernal actors ወይም ደግሞ external sponsors የምንላቸው ደግሞ ውስን ናቸው። በcold war ጊዜ ለምሣሌ ኢትዮጵያን ስትወስድ መንግስት አለ፤ EPLF አለ፣ TPLF አለ ኦነግ አለ፣ ውስን ነበሩ። External sponsor በአንድ ወገን እነ  ሶቪየት አሉ፤ በአንድ ወገን አሜሪካኖች ነበሩ። አሁን እንደዚያ አይደለም። አሁን domestic actors limited ቢሆኑም eventually multiply እያደረጉ ነው የሚሄዱት።ምክንያቱም Bipolar world አይደለም ያለነው። ሁለት ኃይሎች ያሉበት ሳይሆን multiple የሆኑ resource ያላቸው ጂኦፖለቲካል ኢንፍሉዌንሳቸውን ለመጨመር የሚፈልጉ resource ያላቸው አክተሮች ተፈጥረዋል፤ በዓለም ላይ። ስለዚህ አንድ ግጭት ወይም የሕዝብ ለሕዝብ ሲቪል war ሲጀመር እንደ ዱሮ ሁለት መንግስታት አይደሉም የሚገቡት፤ መአት ስፖንሰሮች ይገባሉ። መአት ስፖንሰሮች ስለሚገቡ ሀገር ቤትም ያሉ ውስጥ ያሉ ተዋንያን ቁጥርም እንደዚያው እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ ምክንያቱም ሪሶርሱ ይኖራል...አሁን እኮ ኮንፍሊክት ማፕ አደርጋለሁ ብለህ፣ የሶሪያን ወይንም የየመንን፤ የሊቢያን ብታየው ማን ከማን ጋር እንደሚዋጋ.
..እዚህ ጋ ይሄንን የሚደግፍ፣ በዚያ ጋ ሌላውን ሲወጋ ታያለህ...ኢትዮጵያዊያኖች ይህን እንዲረዱ እፈልጋለሁ። Already ብዙ አጎራባችም ሆኑ የሩቅ ሐይሎች ይሁኑ በተለያያ መንገድ ገብተዋል...”


__________________________________________________


                         የድህረ-ቀዝቃዛ ጦርነት ዘመን ጦርነቶች ልዩ ገፅታ!
                               ጌታሁን ሔራሞ                አምባሳደር ጄፍሪ ፊልትማን እየዋሸን ነው!
  በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆነው አምባሳደር ጄፊሪ ፊልትማን ኖቬምበር 1, 2021፣ የአሜሪካ የሰላም ተቋም ባዘጋጀው መድረክ ላይ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ግንኙነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል። ገለልተኛና ነፃ ተቋም ስለመሆኑ የሚምለው ይህ ተቋም፤ በአሜሪካ ኮንግሬስ አማካይነት የተመሠረተው እ. ኤ. አ. በ1984 ዓ.ም. ነበር።
ታዲያ በዚህ ማብራሪያው ላይ ፊልትማን በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት “Civil War” ስለመሆኑ አስረግጦ ከመግለፁም በላይ ጦርነቱ እልባት ካልተገኘለት ለ20 ዓመታት ያህል ሊዘልቅ እንደሚችል ጥናቶች ያረጋግጣሉ በማለት ለማስረዳት መሞከሩ ይታወሳል።
“Studies show the average modern civil war now lasts 20 years. I repeat: 20 years. A multi-decade civil war in Ethiopia would be disastrous for its future and its people.”
  ጥያቄው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት “Civil War” ነው ወይ? የሚል ነው። በአጭር ቃል ጦርነቱ “Civil War” አይደለም።
የ20ኛውን ክ/ዘመን መገባደጃንና የቀዝቃዛውን ጦርነት ማክተም ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተካሄዱ ያሉ አብዛኞቹ ጦርነቶች ሲቪል ጦርነቶች ሊባሉ እንደማይችሉ ብዙ ጥናቶች ያረጋግጣሉ። ለዚህም በ1980ዎቹና በ1990ዎቹ ለየት ባለ መልኩ ያቆጠቆጠው ግሎባላይዜሽን እንደ አንድ ምክንያት ይቆጠራል። በዘመነ ግሎባላይዜሽን ውጭ/ውስጥ የሚለው ነባር ግድግዳ በእጅጉ ሳስቷል፤ በሀገራት መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ፣ ወታደራዊና ባሕላዊ ትስስር በእጅጉ ናኝቷል። በአንድ ሀገር የሚከሰት የትኛውም ሁነት ሌላውን የመንካት ዕድሉ ከፍተኛ ሆኗል፤ ደሴታዊነት ታሪክ ሆኗል። ስለዚህም ይህን ተከትሎ ጦርነቶችም ቅርፃቸውና ይዘታቸው ተቀይሯል።  ቀድሞ “Civil Wars” ይባሉ የነበሩ ጦርነቶች ወደ ታሪክነት ተቀይረው “Old Wars” የሚለውን ስያሜ ተጎናፅፈዋል።
እናም አምባሳደር ጄፍሪ ፊልትማን የኢትዮጵያን ጦርነት “Civil” ብሎ ሲጠቅሰው ይህን ሳያውቀው ቀርቶ አይመስለኝም። በእንደዚህ ዓይነት ጦርነቶች ዕድሜ መራዘም የአሜሪካ እጅ እንዳለበትም ተሰውሮበት አይደለም። ይልቁን  ዓላማው ጦርነቱን የውስጥ ጦርነት ብቻ እንደሆነ በመጠቆም ላይ ያነጣጠረ ነው። ዓላማው...ጦርነቱ ውስጥ የኛ እጅ የለበትም፤ የናንተው ጣጣ ነው... የሚለውን መልዕክት ማስተላለፍ ነው።
 እንግሊዛዊቷ ሜሪ ካልዶር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካና በማዕከላዊ እስያ የሚደረጉትን ጦርነቶች ቅርፅና ይዘት በተመለከተ በምታደርጋቸው ጥናቶቿ ትታወቃለች።  ጄፊሪ ፊልትማን “Civil War” የሚለውን ስያሜ ለሰጠው ለኢትዮጵያ ጦርነት ሜሪ ካልዶር “New War” የሚለውን ነው የምትመርጠው። የብሪስቶል ዩኒቨርስቲው ፕሮፈሰር ማርክ ደውፊልድ ደግሞ “Postmodern Wars” የሚለውን ስያሜ ይጠቀማል። እንግሊዛዊው ዴቪድ ክን ደግሞ “Informal War” ይለዋል። አሜሪካዊው ፕሮፈሰር  ክሪስ ሄብል ግሬይ “ Virtual Wars and Wars in cyberspace” የሚለውን ስያሜ ሲመርጥ፣ ፍራንክ ሆፍማን ደግሞ “Hybrid Wars” በማለት ይጠራል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ራሺያና አሜሪካ ሶሪያ ውስጥ እያደረጉ ያለው ጦርነት የውክልና ጦርነት (Proxy War) ተብሎ እንደሚጠራ ብዙዎቻችን የምናውቀው እውነት ነው።
ከላይ የጠቀስኳቸው የዘመኑ የጦርነት ዓይነቶች ፊልትማን “Civil War” ብሎ ከጠራው ከበፊቶቹ ጦርነቶች የሚለዩበት አንዱና ዋናው ነጥብ ጣልቃ የሚገቡ የዓለም አቀፍ ተዋንያን መብዛታቸው ነው። እንደ አሜሪካ ካሉ ከምዕራባውያን ሀገራት በተጨማሪ በሌላ ሀገር ጦርነት ውስጥ በልዩ ልዩ ምክንያት (ለምሣሌ በሰብዓዊ ጣልቃ ገብነት) ጣልቃ የሚገቡ ዓለም አቀፍ ተዋንያን ዝርዝር ይህን ይመስላል፦
ዓለም  አቀፍ ዘጋቢዎች
ቅጥር አልሞ ተኳሾች
ሚሊተሪ  አማካሪዎች
ወዶ-ገብ ዲያስፖራዎች
እንደ “USAID, OXFAM, SAVE THE CHILDERRN, HUMAN RIGHTS WATCH, UNHCR, EU, UNICEF, AU, UN” ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት (NGO)
   በእርግጥ ጦርነቱ ጅምር ላይ “Civil War” ሊመስል ይችላል። በቆይታ ግን የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት እየጨመረ ሲሄድ ጦርነቱ ወደ “New War, Hybrid War, Proxy War” ይቀየራል። ለምሣሌ ሊቢያ ውስጥ ጦርነቱ የተቀጣጣለው መነሻ ላይ የአረብ አብዮትን ተከትሎ ቤንጋዚ ውስጥ ወህኒ ውስጥ የነበረ እስረኛ  ጠበቃ እንዲፈታ በሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች በተነሳ ተቃውሞ ነበር። ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል እንዲሉ በዚህ ክፍተት አያሌ “ጅቦች” ሀገሪቷን ሊቀራመቷት ወደ ሊቢያ ተመሙ። አሁን ባለንበት ወቅት በሊቢያ ሰማይ ሥር ፍላጎታቸውን በየፊናቸው የሚያንፀባርቁ ወደ 11 ሀገራት አሉ፤ እነሱም አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ ፣ግብፅ ፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ የአረብ ኢሚሬትስ፣ ራሺያ፣ ኳታር፣ ቱርክና ሱዳን ናቸው። ታዲያ እነዚህ ሀገራት በሙሉ እጃቸውን ያስገቡበት ጦርነት በምን ስሌት ነው “Civil War” ተብሎ የሚጠራው?
በእኛስ ሀገር ቢሆን ምዕራባውያን ለሕወሓት የሳተላይት መረጃን ድጋፍ እየሰጡ ባሉበት ሁኔታ፣ እንደ CNN, BBC, AP, Al Jazeera ወዘተ ያሉ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት ለ24 ሰዓታት በተቀናጀ ሁኔታ በፕሮፓጋንዳና በሐሰት ወሬ ሀገሪቷን እያመሱ ባለበት ሁኔታ፣ ግብፅና ሱዳን ወታደራዊ ሥልጠና እየሰጡ፣ ታጣቂዎችን በድንበር በኩል እያሰረጉ በሚያስገቡበት ሁኔታ፣ USAID, UN እና EU ውግንናቸውን በግልፅ ለሕወሓት በገለፁበት ሁኔታ፣ ጄፍሪ ፊልትማን “ጦርነቱ ‘Civil War’ ነው” በማለት የተሳሳተ ማብራሪያ መስጠቱ ገራሚ ነው። እሱ የጠቀሳቸው አጥኚዎች ሲቪል ጦርነት እስከ 20 ዓመታት ሊራዘም ይችላል ሲሉ ለመራዘሙ አንዱም ሰበብ፣ እንደ አሜሪካ የራሳቸውን ጥቅም አስልተው ጣልቃ የሚገቡ ሀገራት ስለመሆናቸው ሳይጠቅሱ ይቀራሉ?
አሁንስ ቢሆን አሜሪካ ለሕወሓት የሞራልና የሳይበርስፔስ ድጋፍ ከበስተጀርባ እየሰጠች ጦርነቱን ባታቀጣጥለው ኖሮ የጦርነቱ መልክ ዛሬ ምን ይመስል ነበር? አምባሳደር ጄፍሪ ፊልትማን ለ”ሲቪል ጦርነት” መራዘም የጠቀሰው የስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፈሰር  የ”JAMES D. FEARON” ጥናትን ይመስለኛል። የጥናቱ ርዕስ “Why Do Some Civil Wars Last So Much Longer Than Others? ይሰኛል። ታዲያ በዚህ ጥናት ውስጥ ለጦርነቶች ዕድሜ መርዘም ከተጠቀሱት አምስት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ “Support from foreign States” የሚል ነው። ፊልትማን አማፂያንን ደግፎ ጣልቃ በመግባት የጦርነትን ዕድሜ እስከ 20 ዓመታት በማራዘሙ ሂደት የራሱና የሀገሩ የአሜሪካ እጅ እንዳለበት ያልተገነዘብን መስሎት ይሆን?

Read 513 times