Sunday, 12 June 2022 00:00

“በተለይ አስራ አንደኛው” መፅሐፍ ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የደራሲ ይፍቱስራ ምትኩ የበኩር ስራ የሆነው “በተለይ አስራ አንደኛው” የተሰኘ ልቦለድ  መፅሐፍ የፊታችን አርብ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻህፍት ማዕከል ይመረቃል፡፡
ለዋልያ መፅሐፍት አሳታሚ የመጀመሪያው በህትመት የተሣተፈበት ይሔው መፅሐፍ ትኩረቱን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አድርጎ የተፃፈ ሲሆን በምረቃ ስነ ስርዓቱም ላይ አቶ ክቡር ገና፣ ክርስቲያን ታደለ፣ አለማየሁ ገላጋይ  እና ሌሎቹም እንደሚገኙ ደራሲዋ ገልጻለች፡፡
“በተለይ አስራ አንደኛው” ልቦለድ መፅሐፍ በ108 ገፅ ተቀንብቦ በ199 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ዋልያ መፅፍት አሳታሚና ዋልያ መፅሀፍት መደብር ያከፋፍሉታል ተብሏል፡፡


Read 11533 times