Saturday, 25 June 2022 17:59

“ልቤን እንዳትቀብሩት” የግጥም መድበል ሰኞ ይረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


            የሰጥአርጌ አስማረ ሶስተኛ ስራ የሆነው “ልቤን እንዳትቀብሩት” የተሰኘ የግጥም ስብስብ  መፅሐፍ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር በድምቀት ይመረቃል። በእለቱም ግጥም፣ ወግ የመጽሐፉ  ዳሰሳና ከመጽሀፍ የተመረጡ ግጥሞች ለታዳሚ የሚቀርቡ ሲሆን ከምርቃ ስነ-ስርዓቱ ቀደም ብሎ ገጣሚው መጽሀፉን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ገጣሚ መምህርና ጸሀፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ገጣሚና አርቲስት ጌትነት እንየው፣ አርቲስት ጥላሁን ዘውገ፣ ገጣሚ ዶ/ር አንዱአለም  አባተ (የአጸደ ልጅ)፣ አርቲስት  አበባው አስራት  ገዛኸኝ ፀጋው (ዶ/ር)፣ ገጣሚ ረድኤት ተረፈና አርቲስት ሽመላሽ ለጋስ ስራዎቻቸውን እደሚያቀርቡ ታውቋል። “ልቤን እንዳትቀብሩት” የግጥም ስብስብ መጽሀፍ በፖለቲካ፣ በሀገርና በማህበራዊ  ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ከ125 በላይ ግጥሞችን የያዘ ሲሆን በ134 ገጽ ተቀንብቦ በ200 ብርና በ10 ዶላር ለገበያ ቀርቧል። ገጣሚው ከዚህ ቀደም “አሞራና ቅል” የተሰኘ የግጥም መፅሀፍና “የመቅደላ ወርቅ”  የተሰኘ የግጥም  ሲዲ ለአንባቢና ለአድማጭ ማቅረቡ አይዘነጋም።


Read 21532 times