Saturday, 25 June 2022 17:59

“የራስ ብርሃን” መፅሀፍ አርብ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የደራሲና ጋዜጠኛ አሸናፊ ደምሴ ሁለተኛ ስራ የሆነው “የራስ ብርሃን” እና ሌሎች ወገኛ ታሪኮች መጽሐፍ የፊታችን አርብ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ይመረቃል። መጽሀፉ የራስ ምሳሌ የሚሆኑ ታሪኮችን ከሀገር ውስጥና ከዓለም አቀፍ የስነ-ቃል ሀብቶች በመዘነቅ የቀረበ ሲሆን 27 ማራኪ ታሪኮችም ተካትተውበታል።
በነዚህ ታሪኮችም ሀገረኛ ስነ-ቃሎች በወግ መልክ ስለመካተታቸው ደራሲና ጋዜጠኛ አሸናፊ ደምሴ ገልጿል። “የራስ ብርሃንና ሌሎች ወገኛ ታሪኮች” የተሰኘው መጽሀፉ በ160 ገጽ ተቀንብቦ በ200 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በጃዕፈር፣ በእነሆ፣ በኮሜርስ በኤዞፕ መፅሀፍት መደብሮችና በሁሉም የመጽሀፍ አዟሪዎች እጅ ይገኛል ተብሏል። ደራሲና ጋዜጠኛ አሸናፊ ደምሴ ከዚህ ቀደም (በ2007 ዓ.ም) የኢህአዴግ የማሪያም መንገድ” የተሰኘ  የወግ መጽሀፍ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም።

Read 23326 times