Saturday, 25 June 2022 20:35

ውሻውና አጥንቱ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ውሃ የተጠማው ቁራ

          ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ቁራ ረዥም ርቀት ከበረረ በኋላ ውሃ ይጠማውና በጫካ ውስጥ ውሃ መፈለግ ይጀምራል። በመጨረሻም ግማሽ ድረስ በውሃ የተሞላ ማሰሮ ያያል፡፡ ከማሰሮው ውስጥ ሊጠጣ ሲሞክር ግን በመንቆሩ ሊደርስበት  አልቻለም፡፡ ከዚያም መሬት ላይ ጠጠሮች ተመለከተ፡፡ አንድ ሃሳብ መጣለት፡፡  አንዳንድ ጠጠር ወደ ማሰሮው ውስጥ መጣል ጀመረ፡፡ ውሃው ወደ ማሰሮው አንገት ጋ ሲደርስለትም፣ አጎንብሶ እስኪበቃው ድረስ ጠጣ፡፡ የተጠማውን ያህል ረካ፡፡
ውድ ልጆች፡- ከዚህ ታሪክ የምንማረው ቁምነገር፤ በደንብ ካሰብንበት መፍትሄ የማይገኝለት ችግር እንደሌለ ነው፡፡ ፍላጎቱ ወይም ፈቃዱ ካለ መንገዱ ወይም መላው አይጠፋም ይባላል፡፡  




Read 2452 times