Friday, 08 July 2022 00:00

የዶላር እጥረት የሀጂ ተጋዦችን አደናቀፈ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

ዘንድሮ ለጉዞው ፈቃድ ከተሰጣቸው 19600 ሰዎች መካከል ወደ መካ የተጓዙት 3 ሺዎች ብቻ ናቸው፡፡
በየዓመቱ የሀጂና ኡምራ ሃይማታዊ ስርዓትን ለመፈፀም ወደ መካ የሚጓዙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድሮ ከፍተኛ የዶላር እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት ሳይጓዙ ቀሩ፡፡ ዘንድሮ  ለጉዞው ፈቃድ ከተሰጣቸው 19600 ተጓዦች መካከል ሶስት ሺህ ያህሉ ብቻ ወደ ስፍራው ተጉዘዋል፡፡
ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በዚህ ሃይማኖታዊ ስርዓት ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡ ሰዎች ዕድሉ እንዳልተሳካላቸው  ታውቋል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በአገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ  እጥረት  እና በመጅሊሱ ውስጥ ተከስቷል የተባለው አስተዳደራዊ ችግር እንደሆነም ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ወደ ሳውዲ አረቢያ መካ በመጓዝ የሀጅና ኡምራን ሃይማኖታዊ ስርአት የሚፈፅሙበት ይኸው ስነ ስርዓት ባለፉት 2 ዓመታ  በኮቪድ 19 ወረርሽኝ  ሳቢያ ተቋርጦ ቆይቶ ዘንድሮ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

Read 9657 times