Saturday, 23 July 2022 14:21

የቁም ፅሕፈት ነገር

Written by  ከነቢይ መኮንን
Rate this item
(1 Vote)

    እንዲህ እንደዛሬው የኮምፒውተር ዘመን ሳይመጣ በፊት ትልቁ የፅህፈት መሳሪያ፣ የመኪና ፅሕፈት፣ ከባዱ የፅሕፈት ሥልጣኔ ነበር፡፡ መኪና
እንግዲህ የታይፕ ማድረጊያ ወይም typewriter መሆኑ ነው፡፡ ማናቸውም፤ ሥልጣኔ ያመጣውን ማሽን መኪና ስለምንል ነው፡፡ “ልብስ ሲቀደድብን ወደ መኪና ሰፊ ቤት ወስደህ አሰፋው” ይባላል”፡፡ የኮሌታ ነገር ሳስብ ሁሌ በአዕምሮዬ የሚመጣ አንድ የሰማሁት ታሪክ አለ፡፡ ስለ አንድ የቱሉ ቦሎ ከተማ መምህር ታሪክ ነው፡፡ ከመምህሩ ታሪክ በፊት ግን፤ ኮሌታ ወይም ኮላር የሚለውን ቃል ትርጉም እንወቅ፡፡ ኮሌታ ወይም ኮላር በእንግሊዝኛ Colet
ወይም collar የሚባለው ነው፡፡ የዌብስተር ኮሌጅ መዝገበ ቃላት ኮላር - “የሸሚዝ፣ የኮት፣ የመጎናፀፊያ የአንገት ዙሪያ ሆኖ ሁሉም ተሰፍቶ የሚገኝ
ነው፡፡ ተነጥሎ በአንገትጌ ጀርባ የሚደረገውን የማጅራት ዙሪያ ድጋፍ ደግሞ ክለሪካ ኮላር (Clerical collar) ይለዋል፡፡ ፈረንሳይኛው ኮሊየ(collier) ይለዋል፡፡ ክራገን (kragen) ነው በጀርመንኛ፡፡ በአማርኛ “ክሳድ” የሚለውን ብናይ ከሳቴ ብርሃን፡- “ከማጅራት ቀጥሎ ያለው የወደኋላ አንገት” ይለዋል፡፡
   ዘርጋው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ደግሞ፡- “ተካሪስ፣ታጣፊ አንገትጌ፡፡ ክራባቱ የሸሚዙን ክሳድ አጠፈው፡፡” ይላል፡፡ በሁሉም ቋንቋ “ከ” የሚለውን ድምፀት መያዙንም ልብ እንበል፡፡ አማርኛው “ ኮሌታ” የሚለው ላይ ጠንቷል፡፡ ስለ-ሥርወ ቃሉ ይሄን ያህል ካልን፣ አሁን ወደ መምህሩ ታሪክ እንመለስ፡፡
የቱሉ ቦሎው መምህር ኮሌታው ከፊት ለፊቱ አለቀበት፡፡ ኮሌታ፣ቶሎ ቶሎ ስለሚቆሽሽና ቶሎ ቶሎ ስለሚታጠብ፣ መታጠብና መፈግፈግ ስለሚበዛበት ያልቃል፡፡ ስለዚህ መኪና ሰፊ ቤት ወስዶ አስገለበጠው፡፡ አሁን ጀርባው ፊት ሆነ እንደማለት ነው፡፡ “የፊተኞች የኋለኞች ይሆናሉ” እንዲል፡፡ “የኋለኞችም የፊተኞች ይሆናሉ” የሚል እሳቤ እንዳለ ያመለክታል፡፡ መምህሩ የጀርባውም ሲያልቅበት አንድያውን ቆረጠውና አረፈው!! ይህንን ታሪክ ያጫወተኝ የጉዳዩ
የዐይን ምስክር የነበረው አባ ጫላ የሚባል ወዳጄ ነው፡፡ አባ ጫላ ሲቀልድ፤ “የኮርያ ኮሌታ- አልባ ኮት የመጣው ከዚህ ሳይሆን አይቀርም፡፡” ይላል፡፡
መምህሩ ይሔንንም የ ኮሌታ ቆረጣና ቅምቀማ በመኪና ነው ያሰራው፡፡ የታይፕ ራይተር የመኪና ፅሐፈት ከመምጣቱ በፊት ፅሕፈት አቋሙ ምን ይመስል ነበር? ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል “የቁም ፅህፈት ሥራ በደንብ ስለመቋቋሙ”  እንዲህ ይሉናል፡፡
  “የቁም ፅሕፈት ሥራ ጥንታዊ ለመሆኑ ምንም ከመፃሕፍት ብሉያትና ከሐዲሳትም ጠቅሶ በዝርዝር ማስረዳት የሚያዳግት ባይሆን ባፄ ዘርዐ ያዕቆብና ከዚያም ወዲህ ቀጥለው በነገሱት ነገስታት ዘመን ተጽፈው በየጊዜው በዋሻ፣ በደሴት፣በገዳማት፣ በአድባራት የሚገኙት መፃሕፍት በቂ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ም ንጊዜም ቢ ሆን እነዚህ ጠ ቃሚ የ ሆኑ መፃሕፍት ባንድ መሥሪያ ቤት ተጠቅለው ባንድ ሃላፊ ሹም አማካኝነት ተገኝተውና ተሠርተው
አያውቁም” ዕውነት ነው፡፡ ይሄ ሀቅ ለቅርሳ ቅርሶቻችንም፣ ለአብያተ-ክርስቲያናት ሀብታትም፣ ለባህላዊ መድኃኒቶቻችንም፣ ለምድር-ከርስ ደንጋያትና
ማዕድናትም ሆነ ለውሃ ሃብት ነብሳትና እንስሳት፤ እንዲሁም ለአየር አዕዋፋትና ገና ላልታወቀ ንብረታችን ሁሉ የሚያገለግለን መርህ ሊሆን ይገባዋል፡፡
ብላቴን ጌታ ማህተመ፣ በመቀጠል፤ ይዘረዝሩልናል፡፡
“የቁም ፀሐፊውም ሥራ በታዘዘ ጊዜ የሚፅፈው አገር ቤት ሄዶ በቤቱ ተቀምጦ ነበር፤ ብራናውም ተፍቆ ተዘጋጅቶ ስለማይሰጠው የመፅሐፉ ትልቅነትና ትንሽነት እየተገመተ ፍየልና በግ ይታረድና ሥጋውን በልቶ፣ ቆዳውን ፍቆ ወይም አስፍቆ ብራና ያዘጋጅ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜም እንዲያግዙት ለጎረቤቶቹ ሥጋውን በልተው ቆዳውን እንዲሰጡት ከተረከበው ከብት ይሰጣቸው ነበር ይባላል፡፡ ኋላ ግን በሥራው ስለታሰበበት ከፈረንጅ አገር ያማረና የፀዳ ብራና እየተዘጋጀ እንዲመጣ ደንብ ሆነ፤ ሠራተኞቹም በ፲ዓለቃ ተጠቃለው ሥራቸውን በተወሰነ ጊዜ ጨርሰው እንዲያስረክቡ ተደረገ። ነገር ግን ሥጋ መብላት በመቅረቱ ፀሃፊዎቹ የሚጎዱ ስለሆነ በዚህ ለውጥ ሌላ ጥቅም ተሰጥቷቸዋል፡፡ ስለ ቁ ም ፅ ሕፈቱም ሥ ራ በ ሠኔ ፲ ፱፻፲፩ ዓ.ም በ ፅሕፈት ሚኒስትሩ ፊ ርማ የ ተሠጠው የስራ ያስተዳደር ደንብ ቀጥሎ የተጻፈው ነው፡፡ ፲፱፻፲፩ ዓ.ም ሠኔ ፶፫ቀን፡፡” ብለው መሰረቱን ጥለው በነቁጥ ያስቀምጡታል፡፡ እኔም አልፎ አልፎ እያልኩ አንዳንዶቹን ላንባቢ እነቁጣለሁ”፡፡ የቁም ፅሕፈት መሥሪያ ደንብ፡፡ “የቁም ፅሕፈት ሥራ በተለይ እንዳንድ ክፍል መስሪያ ቤት መዝገብና ካርኔ፣ መስሪያ ቤትና አሰሪ ተለይቶለት እንዲቆም በንግሥተ ነገስታት ዘውዲቱና በልዑል አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ትዕዛዝ ተፈቅዷል፡፡
   1ኛ
መዥመሪያ የቁም ፅሕፈት መሥሪያ ቤት ሹም መጻሕፍትን ሁሉ በዝርዝር ፅፎ፣ አንዳንዱ መፅሐፍ በምን ያኽል ወርና ቀን እንደሚያልቅ አራት ሰዎች ጨምሮ በጥንቃቄ መገመት አለበት፡፡ የተገመተበትም ወረቀት ተፈርሞ አንዱ በፅሕፈት ሚኒስቴር ጓዳ ይቀመጣል፤ ፪ኛው ለቁም ፅሕፈት መሥሪያ ቤት ይሠጣል፡፡…
    2ኛ
ለቁም ፅሕፈት የሚመረጡት ፀሐፊዎች፤
ሀ/ ዘይቤ የጠነቀቁ
ለ/ ፅሕፈትን ከናገባቡ አጥርተው ያወቁ
ሐ/ የሥራ አለቃቸውም የተማረና መፅሐፍ አቃንቶ ለ ማረም የ ሚችል፤ ፅ ሕፈትም አ ጥርቶ የሚያውቅ፤ሊሆን ይገባዋል፡፡
   3ኛ/
….ቁም ፀሐፊ ለታዘዘው መፅሐፍ በቂ ቀለምና ብራና ይቀበላል፡፡ የታዘዘውን ሲያስረክብም በደብተሩ ላይ ይፈርማል…. ሲያስረክብ ካርኔ ይቀበላል፡፡ መጽሐፉ ትልቅ ከሆነ ስለ ዐይኑ ድካም እስከ አስር ቀን እረፍት ይሰጠዋል…
   4ኛ
በሰዓቱ ባያስረክብ በመጀመሪያ ከቀለቡ ከሦስት አንድ እጅ ይቆረጣል፡፡ በሁለተኛ እኩሌታ ቀለቡ፣ በሶስተኛው ሙሉ ቀለቡ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ባራተኛው ከስራው ይወጣል፡፡
   5ኛ/
ፀሀፊው በሰዓቱ ባለማስረከቡ ቅጣቱ ከቀለቡ ተቆራጭ የሚሆን ነው ብለናል፡፡ የፀሐፊው ቀለብ ተቆራጭ ሲሆን ለመፅሐፍ መግዣ እንጂ ለሌላ አይውልም፡፡ ማስረጃ ካለው ግን ከቅጣት ይድናል፡፡
   6ኛ
ፀሐፊዎች የሚመቻቸው ገለልተኛ ቦታ ሆነው ለመሥራት፣ ፈቃድ ለሥራው ለመጠየቅ ኃላፊውን ያስፈቅዳሉ፡፡ የሚሠሩትን መፅሐፍ በወር በወሩ እያመጡ ማሳየት አለባቸው፡፡
   7ኛ
Progressive report ስለ ሁኔታው የመ/ ቤቱ ሹም በወር በወሩ ለፅ/ሚኒስቴር ሪፖርት ያደርጋል፡፡
   8ኛ
ያለ ፅ/ሚኒስቴር ማዘዣ ማናቸውም ወጪ አይደረግም!...
   9ኛ
በቁም ፅሕፈት መ/ቤት የተሠራ መፅሐፍ ወይም የተገዛና መታያ የገባ ቢሆን የመፅሐፍ ገቢነቱ በቁም ፅሕፈት መ/ቤት ነው፤ የመ/ቤቱ ሹም ወ ይም ወ ኪሉ የ ገባውን መ ፅሐፍ ሁ ሉ በተሰጠው ረቂቅ አርአስቱን ፅፎ ወደ ፅ/ሚኒስቴር አቅርቦ ዕለቱን ያሳትማል፤ ወጪም ሲሆን የታዘዘበትን ማህተም ተቀብሎ “ዘወሀቦውን” (galley- proof እንዲሉ) በተሰጠው ቀን ረቂቅ ፅፎ አሳትሞ ወጪ ያደርጋል እንጂ ሳይታተም ገቢና ወጪ ለማድረግ ክልክል ነው፡፡
  10ኛ
የቁም ጽ/መ/ቤት ሹም ባልደረብነት የሚሠሩ ሠራተኞች፡-
ሀ/ ቁም ፀሐፊዎች
ለ/ ጽላትና ዕጸ- መስቀል ሠራተኞች
ሐ/ የመፅሐፍ ሐረግና ሥዕል ሠዓሊዎች
መ/ መፅሐፍ ደጓሾችና ማኅደር ሰፊዎች
ሠ/ ብራና ሠራተኞች
ረ/ጥቁር ቀለም አውጪዎች
የነዚህ አለቃ የመ/ቤቱ ሹም ነው፡፡
11ኛ
የቁም ፅ/መ/ ሹም ከላይ ከሀ-ረ ከተጠቀሱት ውስጥ አንድ የመ/ቤቱምን ቁልፍ ያዥ እና አንድ የሥራ ረዳት የሚሆነው መርጦ ማድረግ መብቱ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ግን እንደ ወታደር ደንብ የ፻፣፶ አለቃ እያለ ሊያደላድል አይችልም፡፡
12ኛ
ይህ ደንብ በፅ/ሚ/ር ማኅተም ታትሞ ትክክል ግ ልባጩ (copy) ለ ቁም ፅ ሕፈት መ / ቤት ይሰጣል፡፡ ማ ንኛውም ማ ህተም በፅ/ሚ/ር መዝገብ ቤት ይቀመጣል፡፡ ፲፱፻፲፩ ዓ.ም ሠኔ…ቀን ፊርማ ፀሐፊ ትዕዛዝ ወልደ መስቀል



Read 1503 times