Saturday, 23 July 2022 14:30

20ኛውን የዓለም ሻምፒዮና በ2025 ቶኪዮ ታስተናግዳለች

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

     ከ100 በላይ የኦሬጎን22 ተሳታፊዎች በቪዛ ችግር ተስተጓጉለዋል


          የዓለም አትሌቲክስ ምክርቤት ከዓለም ሻምፒዮናው ጋር አያይዞ በኦሬጎን ባካሄደው ጉባኤ በ2025 እኤአ ላይ 20ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን እንድታዘጋጅ የጃፓኗን ቶኪዮ ከተማ እንደመረጠ ታውቋል፡፡ ሌላዋ የደቡብ ኤስያ አገር ሲንጋፑር ሻምፒዮናውን የማስተናገድ እ ድል ማ ጣቷ ብ ዙ ባ ያስገርምም ኬንያ በአፍሪካ ምድር በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮናውን ለማዘጋጀት ያቀረበችውን እቅድ ምክርቤቱ አለመቀበሉ የሚያስተዛዝብ
ይሆናል። በ2025 እኤአ ላይ ሻምፒዮናውን ለማዘጋጀት አገራት ጠንካራ ፉክክር ቢያደርጉም ጃፓን ያቀረበችውን የመስተንግዶ እቅድ ላለመቀበል ያስቸግራል ያሉት ሴባስቲያንኮው ናቸው፡፡ የጃፓን አትሌቲክስ ፌደሬሽን የተመሰረተበትን 100ኛ ዓመት ከ20ኛው የዓለም ሻምፒዮና ጋር አያይዞ ማክበሩ  ይገባል  ብለዋል፡፡ ጃፓን ለሻምፒዮናው መስተንግዶ ማራኪ እቅድ በማቅረብ፤ ለዓለም አትሌቲክስ የተሻለ የገቢ ምንጮችን በመፍጠር እና በአየር ንብረት
ተስማሚነት ተፎካጃሪ የነበሩትን የኬንያዋ ናይሮቢ እና የሲንጋፑር ሴሊሳ ከተሞች በልጣ ተገኝታለች፡፡
   የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ውድድሩን ባስተናገደው የኦሬጎን ዩኒቨርስቲው ሃይዋርድ ፊልድ ስታድዬም፤ በሁሉም የውድድር መደቦች በታየበት ማራኪና ተቀራራቢ ፉክክር፤ በብሮድካስትና በማህበራዊ ሚዲያዎች ባገኘው ትኩረት ደማቅ መሆኑን ማንሳት ይቻላል፡፡ በአስተናጋጇ አገር አሜሪካ በኩል በርካታዎችን ያላስደሰተው ዋናው ጉዳይ ከቪዛ ፖሊሲ ጋር በተያያዘ ውድድሩን በስፍራው ተገኝቶ የመከታተል እድል ፈታኝ ሆኖ ማለፉ ነው፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ አትሌቶች፤ አሰልጣኞች፤ የሚዲያ ባለሙያዎችና ሌሎች የልዑካን ቡድን አባላት በቪዛ መዘግየት፤ ውስብስብ አሰራርና ክልከላ የዓለም ሻምፒዮና ተሳትፏቸው ተስተጓጉሎባቸዋል፡፡ ቪዛ ለማግኘት ከየኤምባሲዎቹ ቆንስላዎች ጋር የሚያደርጉት የቪዛ ቃለምልልስ መጓተት፤ የመስፈርቶች መቀያየር፤ ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዙ የነበሩ መመርያዎች ከፍተኛ ችግሮችን በብዙዎች ላይ ፈጥሯል፡፡ በቪዛው የተቸገሩ በዋናነት በአፍሪካዎቹ አገራት ደቡብ አፍሪካ፤ ኬንያ ፤
ኢትዮጲያ፤ ዚ ምባቡዌ ሌ ሎችም ቢ ጠቀሱም እነጃማይካም ተጎሳቅለዋል፡፡ የዓለም አትሌቲክስ ማህበርን የጠቀሰ ዘገባ እንዳመለከተው ከ100 በላይ አትሌቶች፤ አሰልጣኞች፤ ሌሎች ባለሙያዎች ቪዛ ዘግይቶባቸዋል፤ አጥተዋል ወይም ጉ ዳያቸውን ማ ስፈፀም ባ ለመቻላቸው የዓለም ሻምፒዮና ተሳትፏቸው ተዛብቶባቸዋል። አሜሪካ ለዓለም ሻምፒዮናው ቪዛ በመስጠት ልዩ ስትራቴጂ አለመከተሏን የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሴባስቲያን ኮው ጨምሮ፤ የቀድሞ አትሌቶች፤ የፌደሬሽን ሃላፊዎችና ትልልቅ ሚዲያዎች ኮንነዋል፡፡

Read 953 times