Saturday, 23 July 2022 14:41

የኢትዮጵያ ቡድን በኦሬጎን22

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

  በዓለም ሻምፒዮናው ታሪክ ከፍተኛውን ውጤት ለማስመዝገብ ጫፍ ደርሷል፡፡ በሜዳልያዎች፤ በሪከርዶችና በተለያዩ የውጤት ደረጃዎች ከ48 ሚሊዮን ብር በላይ አግኝቷል፡፡ በአትሌቶቹ ፕሮፌሽናሊዝም ለዓለም ስፖርት ተምሳሌት በሚያደርጉ ሁኔታዎች ገንኖ ወጥቷል፡፡


         18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ ነገው እለት ፍፃሜውን ያገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን ባለፈው ሳምንት ውስጥ በሁለቱም ፆታዎች 3 የወርቅ፤ 4 የብርና 1 የነሐስ በአጠቃላይ 8 ሜዳልያዎች አግኝቷል፡፡ በታሪክ ከፍተኛውን ውጤት የሚያስመዘግብበት እድል ዛሬና ነገ በመካከለኛ እና ረጅም ርቀት የሚካሄዱ ውድድሮች ይወስናሉ፡፡ በ ሻምፒዮናው ዛ ሬና ነ ገ በ ሁለቱም ፆታዎች በ800ሜ በ800 ሜ የፍፃሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡ በ5000 ሜትር በሴቶች ለተሰንበት ግደይ፤ ዳዊት ስዩምና ጉዳፍ ፀጋይ እንዲሁም በወንዶች ሙክታር ኢድሪስ፤ ሰለሞን ባረጋና ዮሚፍ ቀጀልቻ መወዳደራቸው የኢትዮጵያ ቡድን ተጨማሪ ሜዳልያዎች የሚሰበስብበትን እድል ያሰፋዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ሻምፒዮና ታሪክ ከፍተኛውን ውጤት ኦሬጎን ላይ እንድታስመዘግብ
1 የወርቅ 1 የብርና 1 የነሐስ ሜዳልያዎች ከቀሩት ውድድሮች መጎናፀፍ ይጠይቃል፡፡ በ2005 እኤአ በፊንላንድ ሄልሲንኪ የኢትዮጵያ ቡድን 3 የወርቅ፤
4 የብርና 2 የነሐስ በአጠቃላይ 9 ሜዳልያዎች በማግኘት ትልቁን ውጤት ማስመዝገቡ የሚታወስ ነው፡፡
  18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመጠናቀቁ በፊት የኢትዮጵያ ቡድን በሁለቱም ፆታዎች ከሰበሰባቸው 3 የወርቅ፤ 4 የብርና 1 የነሐስ ሜዳልያዎች በተጨማሪ በየውድድሮቹ 2 አራተኛ ደረጃዎች፤ 1 አምስተኛ ደረጃ፤ 2 ስድስተኛ ደረጃዎች፤ 1 ሰባተኛ ደረጃና 2 ስምንተኛ ደረጃዎች በሁለቱም ፆታዎች ተገኝተዋል፡፡ በማራቶን በሁለቱም ፆ ታዎች የ ሻምፒዮናው ሪ ከርዶችንም ተመዝግበዋል፡፡ በ ዚህ ው ጤት መ ሰረት ለ ዓለም ሻምፒዮናው ከቀረበው የሽልማት ገንዘብ የኢትዮጵያ ቡድን ድርሻ 915ሺ ዶላር ላይ ደርሷል። በወቅታዊው የምንዛሬ ዋጋም ከ48 ሚሊዮን ብር በላይ ይገመታል፡፡ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ለወርቅ $70,000፤ ለብር $35,000ና ለነሐስ $22,000 ዶላር ይሸለማል፡፡ ለአራተኛ $16,000፤ ለአምስተኛ $11,000፤ ለስድስተኛ
$7000፤ ለሰባተኛ $6000 እንዲሁም ለስምንተኛ $5000 ይበረከታል፡፡
 በኦሬጎን22 ላይ አትሌቶቻችን በአንፀባራቂ ድላቸው ከማኩራታቸው ባሻገር ለዓለም ስፖርት ተምሳሌት በሚያደርጓቸው ሁኔታዎች ገንነው እናገኛቸዋለን፡፡ ውድድሮችን በቀጥታ የቴሌቭዠን ስርጭት፤ በራድዮ ኮሜንታተሮች፤ በዩቲውብና በማህበራዊ ገፆች በመከታተል ሁላችንም ልንታዘብ የምንችለው ነው፡፡ በዓለማችን ታዋቂ የፎቶግራፊ ድረገፅ የሆነው www.gettyimages. com ላይ የኢትዮጵያን ቡድን ተሳትፎ የሚገልፁ ፎቶዎች መመልከትም ይበቃል፡፡ የኛ አትሌቶች ከድሎቻቸውም በላይ በስፖርታዊ ቁመናቸው፤ ገፅታቸውና አኳኋናቸው ስፖርቱን ለዓለም ህዝብ የሚያስተዋውቁ ሆነዋል፡፡ አካል ብቃታቸው፤
ጀግንነታቸው፤ አሯሯጣቸው፤ የቡድን ስራቸው፤ ተፎካካሪነታቸው፤ የአገር ፍቅራቸው፤ ስፖርታዊ ጨዋነታቸው፤ እምነታቸው፤ ደስታ አገላለፃቸው፤ ግርማ ሞገሳቸው፤ ትህትናቸው፤ ቆራጥነታቸው፤ ጥረታቸው፤ አፍሪካዊነታቸውን በየውድድሩ ለመላው ዓለም ህዝብ አሳይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቶች በታሪክ ከፍተኛውን ውጤት ሊያስመዘግቡ በሚችሉበት ደረጃ ውስጥ ገብተዋል። በሁሉም ውድድሮች ልዩ ፕሮፌሽናዝም ማሳየት ጀምረዋል፡፡ በስልጠናና በውድድር ቁመና ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ይስተዋላል፡፡ አትሌቲክሱ በአጠቃላይ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ልምድ ባደበሩ ባለሙያዎች ስብስብ መጠናከሩንም በተለያየ
አጋጣሚ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የዘንድሮውን ውጤት ልዩ የሚያደርገውም ይህ ነው፡፡ ፎቶዎቹም የሚገልፁትም ይህን ነው፡፡ በ18ኛው የዓለም አትሌቲከስ ሻምፒዮና ስምንተኛ ቀ ን ላ ይ 3 2 አ ገራት አ ንድና ከ ዚያም በላይ ሜዳልያ በማግኘት የሜዳልያ ሰንጠረዠ ውስጥ ገብተዋል፡፡ አሜሪካ 22 ሜዳልያዎች (7
የወርቅ፤ 6 የብርና 9 የነሐስ) በማስመዝገብ ከዓለም የመጀመርያውን ደረጃ ስትይዝ፤ በ8 ሜዳልያዎች (3 የወርቅ፤ 4 የብርና 1 የነሐስ) ከዓለም ሁለተኛ
ደረጃ ይዛለች፡፡ ጃማይካ በ6 ሜዳልያዎች (2 የወርቅ፤ 3 የብርና 1 የነሐስ)፤ ቻይና በ4 ሜዳልያዎች (2 የወርቅ፤ 1 የብርና 1 የነሐስ) እንዲሁም ኬንያ በ6
ሜዳልያዎች (1 የወርቅ፤ 3 የብርና 2 የነሐስ) እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ አከታትለው ይዘዋል፡፡ ከኢትዮጵያና ከኬንያ ውጭ ሜዳልያዎች ያገኙት
ሌሎች የአፍሪካ አገራት ኡጋንዳ 1 ወርቅና 1 ነሐስ እንዲሁም ሞሮኮ 1 የወርቅ ሜዳልያ ድል ነው፡፡       

Read 11166 times