ዝምታ
ዝምታ´ኮ ዘላለም ነው
ግርማ ሞገሱም ልክ የለው።
ጥልቀቱ የትየለሌ፣ ዱካውስ የት ተደርሶበት
በወሸከሬ በሃሜት፣ በእብሪት ምላስስ
ማን ልሶት…
የሰው ከንቱነት መች ነክቶት።
ዝምታማ ቅን ውበት ነው
ምነው ቢሉም፣
አንድም፣ እውነት፣ የጸጥታ መደብር ናት
አንድም እውነት ማለት
የውበት ሰራ- አካላት ናት!
ሁሉም አሉ ዝምታ ቤት።
ዝምታ´ኮ ሰላምም ነው፤ ፍፁም
የለሆሳስ ድባብ
እኛኑ አቅፎ የሚያስሸልብ
ዝምታ´ኮ ትፍስህት ነው
አንዳች እኩያ የሌለው
የርካሽ ኑሯችን ድፍርስ፣ ያልበረዘው
ንፁህ ማይ ነው
ዕምባም´ኮ ዝምታ ነው
ፈገግታም ቢሆን ዝምታ
ፍቅርማ ከሁሉም በላይ፣ እጅግ ሃያል
ዝምታ ነው
ሞትም ነው ፍጻሜ እርጭታ
ምነው ኑሯችን በፀዳ፣ በነጠረ እንደ ዝምታ።
ገጣሚ- እሸቱ ጮሌ
ትርጉም- ነቢይ መኮንን
ምንጭ- ህያው ድምጾች
Published in
የግጥም ጥግ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል