Saturday, 20 August 2022 12:50

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን ለማደራጀት በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ህዝበ ውሳኔ ይካሄዳል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 “የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል”ን ለማደራጀት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔ እንዲያዘጋጅ የፌዴሬሽን ም/ቤት አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን ለብቻው ክልል የመሆን ጥያቄ ያነሳውን ጉራጌ ዞንን ጨምሮ ሌሎች በነባሩ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል እንዲቀጥሉ ተወስኗል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በጋራ ህዝበ ውሳኔ ይመሰርታሉ ተብሎ የሚጠበቁት የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲዮ፣ ኮንሶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ አሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ናቸው።
አዲሱን 12ኛ ክልል ይመሰርታሉ ተብለው  የሚጠበቁት እነዚህ ዞኖችና ወረዳዎች በቀጣይ 3 ወር ጊዜ ውስጥ ህዝበ ውሳኔ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
በየምክር ቤቶቻቸው በጋራ ክላስተር ለመደራጀት ውሳኔ ያሳለፉት ሃድያ፣ ሃላባ፣ ከምባታ ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ የም እንዲሁም በዞኑ ም/ቤት ክላስተሩ በመቃወም ለብቻው የክልልነት ጥያቄ እያቀረበ ያለው የጉራጌ ዞን በነባሩ የደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልልነት አንድ ላይ  እንዲቀጥሉ ተወስኗል፡፡
በ1987 በፀደቀው የኢፌድሪ ህገ-መንግስት፤ መሰረት 56 ብሔር ብሔረሰቦችን በውስጡ አካትቶ በግዙፍ ክላስተር የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ተብሎ የተደራጀው ክልሉ ከህዝበ ውሳኔ በኋላ አራት ቦታ መከፈሉ ይረጋገጣል።
ሲዳማ ክልል፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከለውጡ ወዲህ የተደራጁ ክልሎች ይሆናሉ።


Read 11609 times