Saturday, 27 August 2022 10:45

የወጣቱን መረጃ ወደ ሀገር ማእቀፍ ማስገባት ይጠቅማል፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ኢንጀንደር ኼልዝ የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከሚሰራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ውስጥ ወጣቶች ስለ ስነተዋልዶ ጤና ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በተለይም ሴት ወጣቶች የተለ ያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ የሚያደርግበት አሰራር ያለው መሆኑን ባለፈው እትማችን ለንባብ ብለናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም በአዳማ ፕሮ ጀክቱ ከሚተገበርባቸው ትምህርት ቤቶች ለመጡ ተማሪዎችና መምህራኖቻቸው ስልጠና የሰጠ ሲሆን ሌሎች የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ተወ ካዮችም ተገኝተው ነበር፡፡ በዚህ ስልጠና ላይ ዶ/ር መንግስቱ ተፈራ የኢንጀንደር ኼልዝ ሲኒየር ክሊኒካል አድቫይዘር (የህ ምና ነክ ስራዎች ከፍተኛ አማካሪ) የተመለከቱት ርእስ ነበር። በአጠቃላይ የስነተዋልዶ ጤና ማለት ምን ማለት ነው? የሚለ ውንና በተለይም ከኢትዮጵያ አተረጉዋጎም አንጻር ምንን ያካትታል ወይም ያመላክታል የሚለውን ነበር ዶ/ር መንግስቱ ለሰልጣኞች ያቀረቡት፡፡
አንዲት እናት አርግዛ እስክትወልድ ያለውን እና የጨቅላዎቹንም ጤና እንዲሁም
የጾታዊ ጥቃት እንዴት መከላከል እንችላለን?
ጾታዊ ጥቃትን ተከትለው የሚመጡ ጉዳቶችስ ምንድናቸው?
ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶችም ይሁኑ ወንድ ወጣቶች ምን አይነት ናቸው?
ጾታዊ ጥቃት የሚደርሰው ምንጊዜ ወይንም መቼ ነው?
ጾታዊ ጥቃት የከፋ የሚሆነው መቼ ነው ?
የሚለውን በተለያየ አቅጣጫ ለመወያየት መቻሉን ዶ/ር መንግስቱ ተፈራ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአገራችን ከስነተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ ያለው አጠቃላይ የጤና ሁኔታ እንዴት ይገለጻል የሚለውንም ለመመልከት ተሞክሮአል፡፡ ለምሳሌም፡-
የቅድመ ካንሰር በሽታ መከላከል በኢትዮጵያ ምን ይመስላል?
የቅድመ ካንሰር በሽታን ለመከላከል በኢትዮጵያ በጤና ሚኒስቴር በኩል ምን አይነት ዝግጅት ነበረ?
በትምህርት ቤቶች ይሰጡ የነበሩትን ክትባቶች በሚመለከትም ከተማሪዎች ጋር ውይይት ተደርጎአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ በትምህርት ቤትም ሆነ በተለያዩ ሁኔታዎች ጾታዊ ጥቃት በሚኖርበት ጊዜ ምን አይነት ምላሽ ይሰጣል? የሚለውንና በመንግስትስ ምን አይነት ግብረመልስ አለ የሚለውን ወጣቶቹ እንዲያውቁት የተነሱ ነጥቦች ነበሩ፡፡ በአጠቃ ላይም የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት ማለት ምን ማለት ነው? የሚለውንና  እንዲሁም ያል ተፈለገ እርግዝና ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲሁም ምን ችግር አለ? የሚለውን ሁሉ ከመምህራኑም ሆነ ከተማሪዎች ጋር በአንድ መድረክ ውይይት ተደርጎአል ብለዋል ዶ/ር መንግስቱ ተፈራ በኢንጀንደር ኼልዝ ክሊኒካል አድቫይዘር፡፡
በአዳማ ካነጋገረርናቸው ተሳታፊዎች መካከል በአራዳ ክፍለ ከተማ በዳግማዊ ምኒሊክ መሰናዶ ትምህርት ቤት መምህርት የሆነችው ፍሬህይወት አያና ትገኝበታለች፡፡ መምህርት ፍሬሕይወት እንደገለጸችው… "በምታስተምርበት ትምህርት ቤት ውስጥ የተቋ ቋመው የስርአተ ጾታ ክበብን ክበብ ሆኖ የድርሻውን እንዲወጣ ድጋፉን ያገኘው ከኢንጀንደር ሄልዝ ነው፡፡ ኢንጀንደር ሄልዝ በያዝነው አመት መጀመሪያ ላይም እኔን ጨምሮ አምስት መምህራንን ያሰለጠነ ሲሆን በዚያ ስልጠናም የተለያየ እውቀት አግኝተናል፡፡ ተማሪዎችን በምን መንገድ የተሻለ ማድረግ ይቻላል በሚለው እና በተለይም  በራስ መተማመንን እንዲ ያዳብሩ ከማድረግ አንጻር ብዙ ስራዎችን መስራት ተችሎአል ብላለች መምህርት ፍሬህ ይወት፡፡ በቅድሚያ ሰላሳ ሁለት የቀን ተማሪዎችን የአፍላ ቲም ስልጠና የማሰልጠን እርምጃ የወሰድን ሲሆን በሁለተኛው ዙር ግን አቅምን በማጠናከር የማታ ተማሪዎችን ወደ ሰማንያ ሰባት የሚሆኑትን አሰለጠንን። የቀን ተማሪዎችን ጨምሮ በሁለተኛው ዙር ወደ አንድ መቶ ሀምሳ ተማሪችን ማሰልጠን ተችሎአል። የማታ ተማሪዎች  ግማሾቹ የቤት ሰራተኞች፤ የቀን ሰራተኞች፤ ከገጠር ትምህርት ሳያገኙ ወደ ከተማ የመጡ ስለሚገኙባቸው ስሜታቸውን ወይንም ፍላጎታቸውን ለመግለጽ በእጅጉ የሚቸገሩ ግልጽነትን መዳፈር የማይችሉ ነበሩ፡፡ ከማሰልጠን ባሻገርም ወጣቶቹ የስርአተ ጾታ ክበብ አባላትንም ሆነ የጤና ባለሙያዎቹን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉና ሀሳባቸውን እንዲገልጹ እንዲሁም ቅርበትን ለመፍጠር የስልክ ቁጥር እስከ መስጠት ድረስ ለወጣቶ ቅርብ ነን፡፡ መድረስ ያለብንን ደረጃ ደርሰናል ብለን ባንልም በጣም ቅርብ እና ግልጽ በሆነ መንገድ ከወጣቶቹ ጋር መወያየት ችለናል ብላለች መምህርት ፍሬሕይወት;;
ኢንጀንደር ሄልዝ ትምህርት ቤቶቹ ከጤና ጣቢያዎች ጋር በቅርበት እንዲሰሩ የሚያስችል ትስስርን እንደፈጠረላቸው መምህርትዋ ትመሰክራለች፡፡ ከጤና ጣቢያዎቹ ጋር በምን መን ገድ እንደምንገናኝ እና ምን እንደሚሰሩልን፤ በምን መንገድ መቅረብ እንደሚገባን በግልጽ ተወያይተን የምንሰራበት መንገድ ስለተመቻቸ ወጣቶቹን በግልጽ ለመቅረብ እና ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶልናል ብላለች፡፡ በተቋቋመው የስርአተ ጾታ ክበብ የሚሰጠው አገልግሎት የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ፤ ፒጃማ፤ በመጠባበቂያ የሚቀመጥ ዩኒፎርም፤ የገላ መታጠቢያ አገልግሎት፤ ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው ሕክምና፤ እንዲሁም እረፍት ማድረግ ካስፈለገ የተዘጋጀ አልጋ ጭምር መኖሩን መምህርትዋ ገልጻለች፡፡ አንዲት ተማሪ ባላወቀችው ወይንም ጥንቃቄ ለማድረግ ሳትችል አለዚያም ከእስዋ ጥንቃቄ በላይ በሆነ ምክንያት የወር አበባ ዘልቆ ልብስዋን ቢነካባት ልክ በቤትዋ እንዳለች እንዲመስላት እና ካለስጋት ሁኔታውን ተፈጥሮአዊ ሂደት መሆኑን ተገንዝባ የራስ መተማመንን አዳብራ ትምህርትዋን እንድትቀጥል ሁኔታዎች ተመቻችተውላታል፡፡
በሌላም በኩል በአቅማቸው ትንሽ ደከም ያሉና ማየትና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎችም በብዛት አሉ፡፡ በተለይም መስማት የተሳናቸው በአስተርጉዋሚ አማካኝነት አቅርቦቱን እንዲያገኙ የተቻለውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ በቅርብ ግዜም ከእንጀንደር ኼልዝ ያገኘነው ሌላው ነገር የሞዴስ አሰራር ስልጠና ነው፡፡ ይህንን በመሰልጠናችንም ሞዴስ ቢጠፋ ወይንም ዋጋው ከአቅም በላይ ቢሆን እንኩዋን በምን መንገድ ሰርቶ መጠቀም እንደሚቻል ለወጣቶቹ ስለምናስተምር ችግሩ ይወገዳል የሚል እምነት አለን፡፡ በእርግጥ ብዙው ነገር ጥሩ ነው ሲባል ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ነው ለማለት አይደለም፡፡ በመጠኑም ቢሆን እንደ ችግር ከሚቆ ጠሩት መካከል ወደ ክበቡ ግቡ፤ አንዳንድ አገልግሎትን ታገኛላችሁ ወይም ይህን ትጠቀማላችሁ ሲባሉ ገለል የማለት ሁኔታ መታየቱ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ በእድሜአቸው ምክንያት ስለሆነ እንደጥፋት የማይታይ ይሆናል፡፡ ይልቁንም በጥሩ እና ታጋሽ በሆነ አቀራረብ ለማስረዳት መሞከር ጠቃሚ ሆኖ አግኝተነዋል ብላለች መምህርት ፍሬ ሕይወት…››
ዶ/ር መንግስቱ ተፈራ በኢንጀንደር ሄልዝ ክሊኒካ ከፍተኛ አማካሪ እንደገለጹት በአዳማ በነበረው ቆይታ ተማሪዎቹ ንቁ ተሳትፎ እና እውቀቱ የነበራቸው ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በአገሪቱ ያለውን ሁኔታ ምን ይመስላል ሲባል አንዳንዴ የመደበላለቅ ሁኔታ ይስተዋል ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ መረጃን ለማግኘት በጣም ቀላል በሆነ መንገድ በማህበራዊ ሚድያ እንዲሁም አለም አቀፍ የሆኑ መገናኛ ብዙሀን ጭምር እንደልብ የሚገኙበት ዘመን መሆኑ አይካድም። የጤናም ጉዳይ እንደማንኛውም ርእሰ ጉዳይ እንደልብ የሚነበብ ነው፡፡ ስለሆነም በኢንተርኔት የሚገኙትን ነገሮች ከእኛ ሀገር ሁኔታ ጋር በማያያዝ አጉል አተረጓጎም እንዲ ኖረው የማድረግ ሁኔታ ይታያል፡፡ ይህንን ከባህል ከልማድ ከሞራል ጋር አያይዞ በሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ሳይተረጉሙት ያገኙትን ነገር በራሳቸው የዳሰሳ አካሄድ በመተርጎም የቻሉትንና የመሰላቸውን ያህል እውቀቱ አላቸው ቢባልም አካሄዱ ግን ጠቃሚ ላይሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም በስልጠናው ሂደት የታዘብኩት ነገር ወጣቶቹን ከተለያየ አቅጣጫ ያገኙትን መረጃ በቀጥታ ከስነተዋልዶ አካላት ወይንም ጤና ጋር የማያያ ዛቸው ነገርን ወደ እኛ ሀገር ማእቀፍ ውስጥ የማስገባት የወደፊት ስራ እንደሀገር የሚጠ ብቀን መሆኑን ነው ብለዋል፡፡
በሀገራችን ያሉ ህጎች ምን ይመስላሉ? (በተለይም ከስተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ) እድሜያቸውን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ከትምህርት ቤት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ትምህርቶችን መስጠት ያስፈልጋል፡፡
ተማሪዎችንም ሆነ መምህራንን በሚመለከት ወደፊት ወደተግባር መግባት ያለበት ስራ ያለ ይመስለኛል ብለዋል ዶ/ር መንግስቱ፡፡
ዶ/ር መንግስቱ በስተመጨረሻውም ኢትዮጵያ ትልቅና የብዙ ህዝብ መኖሪያ እንደመሆንዋ በተወሰኑ ድርጅቶች እንደማሳያ የሚወሰዱ ፕሮጀክቶች ጥሩና መንገድ የሚመሩ ቢሆንም  የተፈለገውን ውጤት ያመጣሉ ብሎ ለመገመት ግን ያዳግታል፡፡ ከአጠቃላይ ህዝቡ ቁጥር እንኩዋን ሲታይ አርባ ከመቶ የሚሆነው ወጣቱ ትውልድ ነው። ይሄ ቁጥር በጣም ብዙ ከመሆኑም በተጨማሪ ሁሉም በትምህርት ቤቶች የሚገኝ አይደለም፡፡ የስነተዋልዶ ጤናን ጉዳይ በማስተማሩ ሂደት ሊገኙ ወይም ሊደረ ስባቸው የማይችሉ ብዙ ወጣቶች ካለእድሜ ጋብቻ ከመፈጸም በተጨመሪ የጤናው አገልግሎት የት እንዴት ይሰጣል? የሚለውን በትክክል የማያውቁ እንደሚኖሩ ጥርጥር የለውም። ይህ ደግሞ የአንድ ወይም የተወሰኑ ድርጅቶች ስራ እንዲሆን አይጠበቅም፡፡ ስለዚህ በትምህርት ቤቶችም ሆነ ከትምህርት ውጪ ላሉት ስለ ስነተዋልዶ ጤናና ተያያዥ ነገሮች በተቻለ መጠን እውቀቱን እና አገል ግሎቱን የሚያገኙበት እንዲሁም በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የህይወት አቅጣጫቸውን የሚመሩበትን እንደ ትምህርት እንዲያገኙት የማድረጊያ ዘዴ ቢፈጠር ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ ብለዋል ዶ/ር መንግስቱ ተፈራ በኢንጀንደር ሄልዝ ከፍተኛ ክሊኒካል አማካሪ፡፡

Read 11081 times