Print this page
Saturday, 27 August 2022 11:36

“ወላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ” መፅሀፍ ለንባብ በቃ”

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የቀድሞው የፓርላማ አባልና የአሁኑ  ዲፕሎማት የአቶ አማኑኤል አብርሃም ሁለተኛ ስራ የሆነው “ወላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ“ የተሰኘ መፅሃፍ ለንባብ በቃ፡፡
መፅሀፉ በዋናነት ወላይታ ከጥንት እስከ አሁን የተጓዘበትን ታሪክ፣ባህል፣ሀይማኖትና ስብዕና በዝርዝር የሚያስቃኝ ሲሆን ከሽፋን ስዕሉ ትርጉም ገለፃ ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች በውስጡ መያዙን የመፅሀፉ ደራሲ በመግቢያቸው አስፍረዋል፡፡
በሰባት ዋና ዋና ምዕራፎች የተከፋፈለው መፅሀፉ በ188 ገፅ ተቀንብቦ በ200 ብርና በ18 ዶላር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡ አቶ አማኑኤል አብርሃም ከዚህ ቀደም “የሚድያ ነፃነት በኢትዮጵያ” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃታቸው አይዘነጋም፡፡

Read 11655 times