Print this page
Saturday, 03 September 2022 14:44

“ቴአትር ለሰላም” 3ኛው የቴአትር ፌስቲቫል ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   3ኛው የቴአትር ፌስቲቫል “ቴአትር ለሰላም” በሚል ርዕስ ጳጉሜ 2 እና 3 ቀን  2014 ዓ.ምበብሄራዊ ቴአትርና በኤሊያና (ሆቴል እንደሚከበር የቴአትር ባለሙዎች ማህበር አስታወቀ። በመክፈቻው ዕለት ጠዋት ከ3፡00 ጀምሮ “የኮከቡ ሰው” ቴአትር በብሄራዊ ቴአትር በነጻ ለተመልካች ከቀረበ በኋላ ከሰዓት በኋላ በኤሊያና ሆቴል በዚሁ ቴአትር ላይ ጥናት እንደሚቀርብና ከቴአትሩ ተዋንያን ጋር በቀጥታ ውይይት እንደሚካሄድ አርቲስት ቢንያም ወርቁ ለአዲስ አድማስ ገልጿል። በፌስቲቫሉ በሁለተኛው ቀን ማለትም ሀሙስ ጳጉሜ 3 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ የማንያዘዋል እንደሻው ስራ የሆነው “እምዬ ብረቷ” ቴአትር በነጻ ለተመልካች ከቀረበ በኋላ በኤሊያና ሆቴል በምሳ ግብዣ እንደሚጠናቀቅ የገለጸው ማህበሩ በሁለቱም ቀናት ቴአትሮቹን በነጻ መመልከት ለሚፈልጉና በውይይቶቹ ላይ ለሚሳተፉ የብሄራዊ ቴአትርና የኤሊያና ሆቴል በሮች ክፍት መሆናቸውን የቴአትር ባለሙያዎች ማህበር አስታውቋል።

Read 11893 times