Saturday, 10 September 2022 20:59

እንኩዋን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ፡፡ እንኩዋን ለ 2 ሺህ 15 ዓመተ ምህረት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

መጪው ዘመን የሰላም……….የጤና………..የእድገት……….እንዲሆን የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ESOG ይመኛል


       የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ትብብር እንደ ውጭው አቆጣጠር በ1992 ዓ.ም የተቋ ቋመ ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ሲቋቋምም አላማው አድርጎ የተነሳው የእናቶችን እና ጨቅላዎችን ጤንነት እና ሕይወት ለማዳን አስፈላጊውን የስነተዋልዶ ጤና ድጋፍ ለማድረግ ነው፡፡
የስነተዋልዶ ጤናን በሚመ ለከት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን አሰራር ለማጎልበት እንዲቻል የጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎችን አገልግሎት ለማስፋት የሚያስችለውን ቴክኒካል እገዛ ማድረግም ከማህበሩ አመሰራረት አላማ መካከል ነው፡፡ በመሆኑም ላለፉት 30 አመታት በስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ አባላቱን ያሳተፈ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ መደረጉን ማህበሩ በ30ኛው አመታዊ ጉባ ኤው ለአባላቱ ይፋ አድርጎአል፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የተለያዩ የስነተዋልዶ ጤና  ፕሮግራሞችን እውን የሚያደርገው በዋናነት ከኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር እና ከሌሎችም ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ነው፡፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ካከናወናቸው አበይት የስነተዋልዶ ጤና ፕሮግራሞች መካከል ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ፤በወሊድ ጊዜ የደም መፍሰስ እንዳይከሰት ማስቻል፤ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው የተሟላ ድጋፍ ማድረግ ….ወዘተ እና የተለያዩ ብሔራዊ የህክምና መመሪያዎችን (National Guide Line) ማዘ ጋጀትንም ይጨምራል፡፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ESOG በእናቶችና ጨቅላ ህጻናት የስነ ተዋልዶ ጤና ፤ኤችአይቪ ኤይድስ እና ጾታ ዙሪያ በርካታ ስራዎችን የሚ ሰራ ማህበር ነው፡፡ ህክምናውን ከመስጠት ባሸገርም ህብረተሰቡ ጤናውን በተመለከተ አስቀድሞ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መረጃ በመስጠት ንቃተ ህሊናውን መገንባት አስፈላጊ በመሆኑ በመገናኛ ብዙሀንም መልእክትን ያስተላልፋል፡፡
ESOG በተለይም በመገናኛ ብዙሀን ሴቶችን ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም በሚመለከት ሊዳሰሱ የሚገባቸውን የስነተዋልዶ ጤና ጉዳ ዮች ይዳስሳል፡፡
ESOG በህክ ምናው ዘርፍ ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር በመገናኛ ብዙሀን የሚሰሩትን ጨምሮ በተለያዩ ክልል መስተዳድሮች ለሚገኙ የጤና ተቋ ማት ለባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠናን ጨምሮ የተለያዩ ቴክኒካዊ እገዛ ዎችን ያደርጋል፡፡
ESOG በ2014 ከሰራቸው ስራዎች ለማሳያ አንዱን ልናስታውስ ወደድን ፡፡  
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በኢትዮጵያ በግጭት ላይ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም እናቶች እና ህጸናት የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን በምን መንገድ እያገኙ ነው የሚለውን ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በአካባቢዎቹ በመዘዋወር ለመ መልከት ሞክሮአል፡፡
የሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት መጉዋደል ለብዙዎች ህይወት መበላሽት ምክንያት መሆኑ በግልጽ የታየበት ነበር፡፡
በዚህም ብዙዎች የተገድዶ መደፈር ጥቃት ተፈጽሞ ባቸዋል፡፡
እርጉዝ የሆኑ እናቶች በስደት ረጅም መንገድ ከመጉዋዝ በተጨማሪ ምንም የህክምና አገልግሎት በሌለበት ደህንነታቸው ባልተጠበቀ ሁኔታ ልጆቻቸውን መገላገላቸውን የሚያሳዩ ምስክርነቶች ነበሩ፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በጋራ አብሮአቸው ከሚሰ ራባቸው አካላት ማለትም ከፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፤ከክልል ጤና ቢሮዎች እንዲሁም ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ግጭቱ በተስ ፈፋባቸው አካበቢዎች በመሆን የስነተዋ ልዶ ጤና አገልግሎቱ እንዳይ ቋረጥ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ማህበሩ 30ኛ አመቱን ባከበረበት ወቅት የካቲት 14-15/2014 በጉባኤው ላይ ተገልጾ ነበር፡፡
ከአሁን ቀደም በነበረው ግጭት ከተጀመረ በሁዋላ በሰሜኑ የአገራችን ክፍሎች ከደብረ ብርሀን እስከ ቆቦ ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች የጤና ተቋማትን መልሶ ማብቃት በሚያስችል ሁኔታ ለማገዝ እና የወሊድ መሳሪያ ዎች፤የህክምና ግብአቶችን ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በየሆስፒታሎቹ የማድረስ ስራ ተሰርቶአል ፡፡ ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ያለውን የስነተዋልዶ ጤናና የእናቶች ጤን ነትን በሚመ ለከት ትኩረት እንዲሰጥ አስፈላጊ እንደመሆኑ እናቶች እና ሕጻ ናት ምንም ችግር እንዳይደር ስባቸው ሲባል ቀደም ሲልም ግጭቱ እንደ ተጀ መረ  በመቀሌ ካሉ የማህበሩ አባላትና የጤና ተቋማት ጋር በመተ ባበር በስነ ተዋልዶ ጤናና በእናቶች ጤንነት ዙሪያ አገል ግሎት ላይ የሚውሉ ድጋፎ ችንም ማህበሩ አድርጎ እንደነበር በ30ኛው አመት ጉባኤ  ላይ ተገልጾአል ፡፡
በመቀጠልም እስከ አፋር ድረስ በመዝለቅ በተለያዩ ጊዜያት እስከ ዘጠኝ ሚሊ ዮን ብር የሚገመት የስነተዋ ልዶ ጤና ሕክምናን እና የእናቶችን ጤን ነት የሚረዱ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ እንዲደረግ አስችሎአል፡፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር
ወደፊትም                ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆንና የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት እንዲሁም
 የመላው ህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት እንዲጠበቅ ምኞቱን ይገልጻል፡፡  



Read 10411 times