Saturday, 17 September 2022 13:22

“ ወላይታ በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ” መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የቀድሞው የፓርላማ አባል የአሁኑ ዲፕሎማት አቶ አማኑኤል አብርሃም ሁለተኛ ሥራ የሆነው “ወላይታ በዘማናዊቷ ኢትዮጵያ” መፅሀፍ ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኙት አብርሆት የህዝብ ቤተ መፃህፍት ይመረቃል፡፡ በዕለቱ የመፅሀፍ ዳሰሳና ሌሎች ኪነ ጥበባዊ ክንውኖች የሚካሄዱ ሲሆን ከመፅሀፉ የተመረጡ ክፍሎች በታዳሚ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንደሚነበብም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዕለቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ፤ የደራሲው ወዳጅ ዘመዶች፤ ደራሲያንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲገኙም ለማወቅ ተችሏል ደራሲው ከዚህ ቀደም “የሚዲያ ነፃነት በኢትዮጵያ” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃታቸው አይዘነጋም፡፡

Read 21451 times