ላለፉት 20 ዓመታት በልጆች ንባብ ላይ በመስራት የሚታወቀው “ኢትዮጵያ ሪድስ”፣ ሦስተኛውን ዓመታዊ የልጆች ንባብ ጉባኤ፣ “በንባብ ልምድ የዳበረ የልጅነት ዕድገት” በሚል መሪ ቃል፣ ከትላንት በስቲያ ሐሙስና ትላንትና በሳፋየር አዲስ ሆቴል አካሄደ፡፡
በመርሐግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ- መጽሐፍትና ቤተ - መዘክር ኤጄንሲ( ወመዘክር) ፣ የልጆች መጽሐፍት ደራሲዎች ፣ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በጉባኤው በትምህርት ሚኒስቴርና በዩኤስአይዲ የተሰራው የልጆች የንባብ ክህሎት ምዘና 2021 ጥናት፣ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ምዘናና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ኢፋ ጉርሙ የቀረበ ሲሆን፤ በልጆች የንባብ ባህል ልምድ ላይም ውይይት ተደርጓል።
አዲሱ የትምህርት ካሪኩለም የልጆችን የንባብ ልምድ ከማዳበር አንጻር ምን ይመስላል የሚለው በትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ቀርቧል።
በታዋቂ ደራሲዎች የተጻፉና በ”ኢትዮጵያ ሪድስ” የታተሙ የልጆች መጽሐፍት ምረቃ የጉባኤው አካል ነበሩ። የህይወት ዘመን የልጆች መጽሐፍት ንባብ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰብና ደራሲዎችም እውቅና ተሰጥቷል።
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል