Wednesday, 19 October 2022 00:00

የዘንድሮውም ምኞታችን፣ ሰላም መፍጠርና የዋጋ ንረትን መግታት!

Written by  ዮሃንስ ሰ
Rate this item
(0 votes)

በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንሹራንስ ወር በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ሲሆን በሌላ በኩል ጀነራል ኢንሹራንስ ብሮከርስ የተመሰረተበትን 25ኛ የብር ኢዮቤልዩ በዓል እያከበረ መሆኑ ታውቋል።
ጌጤነሽ ኃ/ማሪያምና ብርሃን ተስፋዬ ኢንሹራስ ብሮከርስ የህብረት ሽርክና ማህበር (GIB) የተመሰረተበትን 25ኛ የብር ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ ከዘርፉ ተዋንያን ጋር የኢንሹራስ ወርን በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማክበር አቅዶ ወደ እንቅስቃሴ መግባቱን የጀነራል ኢንሹራስ ብሮከርስ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጌጤነሽ ኃ/ማሪያም ከዘርፉ የተለያዩ ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ባለፈው ረቡዕ ጥቅምት 2 በኢሊሌ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
የኢንሹራንስ ዘርፍ በሀገራችን ስራ ከጀመረ ረጅም ዓመታን ቢያስቆጥርም፤ የዕድሜውን ያህል ለውጥ እንዳላመጣ የተገለፀ ሲሆን፣ ለዚህም የኢንሹራንስ ህጎችና ፖሊሲዎች፣ የዘርፉ ተዋንያን አለመቀናጀት፣እንዲሁም ማህበረሰቡ ስለኢንሹራንስ ያለው ግንዛቤ ማነስና ሌሎችም ችግሮች እንደ ተግዳሮት ተጠቅሰዋል።
እስከ ጥቅምት 26 በሚዘልቀው የኢንሹራንስ ወርም ከዘርፉ እንቅፋቶች ጋር የተያያዙ  ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይቶችን ተገልጿል።
ለኢንሹራሱ ዘርፍ ለውጥ አለማምጣት ሌሎች ተግዳሮቶችም ተነስተዋል፡፡ ለምሳሌም ፡-  የኢንሹራንስ ህግና አዋጅ በእንግሊዝኛ ቋንቋ መፃፍ፣ በኢንሹራንስ ገቢዎችና በአገልግሎት ሰጪዎች መካከል ያለው የተግባቦት ክፍተትና በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው የግንዛቤ ማነስ፤ እንዲሁም የህጉ ውስብስብነት ይጠቀሳሉ፡፡ በሌላ በኩል ሰዎች መድህን (ኢንሹራንስ) የሚገቡት አስገዳጅ በሆኑት ጥቂት የመድህን አይነቶች ብቻ መሆኑም የዘርፉን ዕድገት እንደገደበው ተጠቁሟል፡፡ በኢንሹራንስ ዘርፍ ለውጥ ለማምጣትም በGIB ተነሳሽነት የተጀመረው የኢንሹራንስ ወር ቀጣይነት እንዲኖረው የዘርፉ ተዋንያን ተቀናጅተው መስራት እንደሚኖርባቸው፤ የኢንሹራንስ አካዳሚ መቋቋም እንዳለበትና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከሚዲያ ተቋማት ጋር በቅርበት መስራት እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡ ከተለያዩ የኢንሹራንስ ተቋማት የመጡ ከፍተኛ አመራሮች በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተሳተፉ ሲሆን ከነዚህም መካከል የአዋሽ ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጉዲሳ ለገሰ፤የኢትዮጵያ የመድህን ሰጪዎች ማህበር ፕሬዚደንት አቶ ያሬድ ሞላ፤ የኢንሹራንስ ብሮከርስ ማህበር ፕሬዚደንት አቶ ውበቱ ወርቅነህ፤ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ መሃሪ፤የኢትዮጵያ ጠለፋ መድህን አክሲዮን ማህበር የስትራቴጂና የቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍቅሩ ፀጋዬና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡ ማህበረሰቡ አስገዳጅ ከሆኑት ውጪ ያሉ ከ40 በላይ የመድህን አይነቶችንና ምንነታቸውን ተረድቶ እንዲጠቀምባቸው በርካታ ስራዎችን መስራት ይጠበቃልም ተብሏል፡፡ በተለይ የህይወት መድህንን መተመለከተ ማህበረሰቡ በቂ ግንዛቤ ስለሌለው እስካሁን የህይወት መድህን ለዘርፉ ያለው አበርክቶ አናሳ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ሰው በቀን ከሚጠጣው ማኪያቶ አንዱን በመተውና በመቆጠብ የህይወት መድህን መግባት እንደሚችልና ይህንን ያህል ቀላል እንደሆነ የኢትዮጵያ መድህን ሰጪዎች  ማህበር ፕሬዚደንት አቶ ያሬድ ሞላ ጠቁመው፤ ይህንን ሁሉ እንድንገልፅ ይህን መድረክ የፈጠረችልንን የጌጤነሽ ኃ/ማሪያምና ብርሃን ተስፋዬ የኢንሹራንስ ብሮከርስ የሽርክና ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚዋን ወ/ሮ ጌጤነሽ ኃ/ማሪያምን አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡
በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው ይህ የኢንሹራንስ ወር ፤እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ እንደሚቀጥልም ታውቋል፡፡

Read 6380 times