Print this page
Saturday, 29 October 2022 11:14

ዳሸን ባንክ ከታክስ በፊት 3.8 ቢ. ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 3.8 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን  ያስታወቀ ሲሆን፤ ይህም ካለፈው  ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ57 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተመልክቷል፡፡
ባንኩ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም ከትላንት በስቲያ ሐሙስ በሸራተን አዲስ ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለባለአክሲዮኖች አቅርቧል፡፡
 በ2014 በጀት ዓመት  16.7 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን የገለጸው  ባንኩ፤ አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ22.4 በመቶ ዕድገት እንዳለው  ተጠቁሟል፡፡
ይህም አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን ወደ 91.2 ቢሊዮን ብር ያሳደገው ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 5.9 ቢሊዮን ብር የተገኘው ከወለድ ነፃ አገልግሎት ዘርፍ መሆኑ ተመልክቷል፡፡  
የባንኩ የማበደር አቅም ወደ 79 ቢሊዮን ብር ያደገ ሲሆን፤ የባንኩ አጠቃላይ ሃብትም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ24 በመቶ ዕድገት በማሳየት፣ 117.14 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተነግሯል፡፡
 የባንኩ ባለአክሲዮኖች ድርሻም ወደ 14.4 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ42 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ ባለአክሲዮኖቹ ባለፈው ጉባኤያቸው ተጨማሪ ካፒታል ለማቅረብ መወሰናቸውን ተከትሎ፣ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል መጠንም 7.5 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተገልጿል፡፡

Read 1434 times
Administrator

Latest from Administrator