በደራሲ ወርቅዬ ደምሴ የተጻፈው “የዓይን፣ የጆሮና የአዕምሮ ምስክር” የተሰኘው በግብረገብና ስነምግባር ላይ አተኩሮ የተዘጋጀው መጽሐፍ ለንባብ በቃ።
መጽሐፉ በሰው ልጅ አስተሳሰብና ማንነት ላይ ትኩረቱን አድርጎ፣ የሃገራችንን ጥንታዊና ሐይማኖታዊ የስነምግባር አስተምህሮን መሰረት በማድረግ፣ ባሁኑ ወቅት ያለውን የሐገራችንን ማህበራዊ ኑሮ ከዘመናዊው ዓለም ጋር እያነጻጸረ የሚያሳይ እንደሆነ ታውቋል፡፡
“የዓይን፣ የጆሮና የአዕምሮ ምስክር” መጽሐፍ፣ ደራሲው ከትምህርትና ከረዥም ዘመን የስራ ልምድ ያገኙትን ዕውቀት አቀናጅተው ያሰናዱት ነው ተብሏል።
መጽሐፉ 12 ምዕራፎችና 554 ገጾች ያሉት ሲሆን፤ ዋጋው 250 ብር ነው፡፡
ደራሲው፣ በ1990 ዓ.ም “የፍቅር ጀርባው” የተሰኘ ረጅም ልብ ወለድ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወቃል፡፡
Saturday, 29 October 2022 12:33
የዓይን፣ የጆሮና የአዕምሮ ምስክር” ለንባብ በቃ
Written by ናፍቆት ዩሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና