Sunday, 30 October 2022 00:00

ስለክሩዝ ሚሳይሎች በጥቂቱት”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የጦርነት እና የዉጊያ ነገር ሲነሳ ስማቸው አብሮ ይነሳል። እነኚህን መሳሪያ የታጠቁ ሀገራትን ለወዳጅነት እንጂ ለጠብ የሚያጫቸው የለም። እንደው ከአቅም በላይ በሆነ ገፊ ምክንያት ከነዚህ ሀገራት ጋር ወደ ጠብ ውስጥ ቢገባ እንኳን ሁለቴ እና ሶስቴ የኃይል ሚዛንን ማስላትን ይጠይቃል። ምክንያቱም የታጠቁት መሳሪያ ባህር ተሻግሮ የሚያዳፍነው ክሩዝ ሚሳየል ነውና!
ክሩዝ ሚሳየል አብራሪ የሌለው አነስተኛ አውሮፕላን ነው ማለት ይቻላል። ባለ ቱርቦፋን ሞተሩ እና 6.25 ሜ የሚረዝመው ክሩዝ ሚሳየል፣ 2.61ሜ. የክንፍ ርዝመት ሲኖረው፣ በከፍተኛ ደረጃ ተቀጣጣይ የሆኑ እስከ 450 ኪ.ግ. የሚመዝኑ ቦምቦችን ተሸክሞ፣ ከ800-1600 ኪ.ሜ ርቀት፣ በሰዓት 880 ኪ.ሜ በሆነ ፍጥነት (cruising speed ) መምዘግዘግ እና ኢላማውን መምታት የሚያስችል አቅም አለው።
አንድ ክሩዝ ሚሳየል በጠቅላላው 1450 ኪ.ግ ክብደት ሲኖረው፣ ከዚህ ውስጥ 65 ኪ.ግ የሚሆነው የሞተሩ ክብደት ሲሆን ወደ 450 ኪ.ግ የሚሆነው ደግሞ የሚጭነው ነዳጅ ክብደት ነው። solid rocket booster የተባለው አስወንጫፊው አካል ደግሞ 250 ኪ.ግ የሚሆነውን ክብደት ይይዛል።
የታቀደለትን ኢላማ በመምታት በኩል ክሩዝ ሚሳየል ባለ ንስር አይን መሳሪያ ነው። 1000 ኪ.ሜ ከተምዘገዘገ በኋላ እንኳን የተላከበት የማይረሳው ይህ መሳሪያ፤ “It can fly 1,000 miles and hit a target the size of a single-car garage.” የሚል ምስክርነት ተሰጥቶታል። ይህም ብቻ አይደልም፤ ክሩዝ ሚሳየል ከራዳር እይታ ውጪ በሆነ ዝቅተኛ ከፍታ መጓዝ ስለሚችል በቀላሉ ሊመታና ሊከሽፍ አለመቻሉ መሳሪያውን እጅግ ተወዳጅ እና ተመራጭ ያደርገዋል። ይህን መሳሪያ ኢላማውን በተገቢው መንገድ እንዲመታ የሚያግዙ አራት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ስርዓቶች (systems) አሉ። እነሱም….
IGS - Inertial Guidance System
Tercom - Terrain Contour Matching
GPS - Global Positioning System
DSMAC - Digital Scene Matching Area Correlation
በመባል ይታወቃሉ። እነኚህ አራት የቴክኖሎጂ ስርዓቶች የተለያየ ሚና ሲኖራቸው ክሩዝ ሚሳይሉ ከተተኮሰበት ቅጽበት ጀምሮ ኢላማውን በትክክል እስኪመታ ድረስ በመተባበር ይሰራሉ። የነዚህ የቴክኖሎጂ ስርዓቶች ዋነኛ ሚና የሚሳየሉን ፍጥነት መቆጣጠር፣ ሚሳይሉ የሚምዘገዘግበት መልከዓምድር በመለየት የሚሳይሉን የጉዞ መንገድ እና ሁኔታ መቀየስ፣  የሚሳየሉን የጉዞ ሁኔታ መከታተልና ሚሳይሉ የታቀደለትን ኢላማ በአግባቡ መምታቱን ማረጋገጥ ነው።
ክሩዝ ሚሳየሎች በዓይነታቸው ብዙ ሲሆኑ፤ ከባህር ሰርጓጅ መርከቦች፣ ከተዋጊ አውሮፕላኖች እንዲሁም ከምድር ላይ ሊተኮሱ ይችላሉ።

Read 3168 times