Saturday, 29 October 2022 12:40

በበጎ አድራጎት የBBCን እውቅና ያገኙት ኢትዮጵያዊ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በታላቅዋ ብሪታንያ መዲና ለንደን ላይ ሲኖሩ፣ ሰላሣ ዓመታትን ያስቆጠሩትና ሰሞኑን በብሪታንያ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን BBC ከፍተኛ እውቅናን ያገኙት አቶ ምንተስኖት መንገሻ፤ ሰሞኑን በአዉሮጳ በተለይም በብሪታንያ ጋዜጦችና ብዙኃን መገናኛዎች እየቀረቡ ተሞክሯቸውን እያጋሩ  ነው። ይህን ነገር ለመታወቅ ብለው  እንዳልሰሩትም ይናገራሉ።
በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት ያገለገሉትና በአሁኑ ወቅት በአንድ ኮሌጅ ዉስጥ መምህራንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት አቶ ምንተስኖት፤ በለንደን በሚኖሩ በርካታ ታዳጊ ህጻናት ላይ የሚታየው ድህነት እየጨመረ መምጣቱ ተናግረዋል። የኮሮና ወረርሽኝ በዓለማችን መሰራጨት ከመጀመሩ ከወራቶች በፊት፤ ከሦስት ዓመታት ገደማ በፊት መሆኑ ነዉ፤ አቶ ምንተስኖት ለህክምና ወደ  ዶክተር ጋር ሄደው መቆያ ክፍል ውስጥ  ተራቸዉን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ ፣ አንድ ከአባቱ ጋር የነበረ  የአገሬዉ ታዳጊ ህጻን፣ የተቦረተፈ ጫማ አድርጎ ጣቶቹ ወጥተው በማየቴ ልቤ ተሰበረ ይላሉ። በዚህም ይህን ልጅ በመርዳት ቢያንስ መንፈሴን ማደስ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ ሲሉ አጫውተውናል። በዚህም ነው እ ርዳታ ለማሰባሰብ የባዶ እግር ጉዞ አድርገው፣ ብር አሰባስበውና ገንዘቡን ለርዳታ ሰጭዎች በመስጠት ድሃ  ታዳኂ ህጻናትን ለመደጎም የወሰኑት።
 ሰባት ሚሊዮን ያህል ህዝብ በሚኖርባት በለንደን ከተማ የታዳጊ ህጻናት ድህነት እጅግ አይሎ እንደሚታይ አቶ ምንተስኖት ተናግረዋል።አቶ ምንተስኖት ይህን ሰብዓዊ ስራ በመፈፀማቸው እውቅና ማግኘታቸውን ተናግረዋል። በብሪታንያ በተለይም በለንደን የተለያዩ ጋዜጦችና ብዙኃን መገናኛዎች  ኢትዮያዊው ምሁር ስላበረከቱትና ስላሳዩት ሰብዓዊነት ሰሞኑን በአርአያነት እያነሱ በስፋት ዘግበዋል። ከብሪታንያው ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን ቢቢሲም የእውቅና ሽልማትን አግኝተዋል።
(ቢቢሲ)

Read 1495 times