Saturday, 29 October 2022 18:31

የቤት ሠራተኛዋ ቀጣሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድላ ተሰወረች

Written by 
Rate this item
(5 votes)

•  ተጠርጣሪዋ በፖሊስ እየታደነች ነው ተብሏል

ቦታው እዚህ አዲስ አበባ፣ አስኮ አዲሱ ሰፈር አካባቢ ነው፡፡ ትናንት ከቀኑ 5 ሰዓት ገደማ ሲሆን፤ አንዲት የቤት
ሠራተኛ  ቀጣሪዋን በአሰቃቂ ሁኔታ፣ በቢላና በዘነዘና ገድላ መሰወሯን፣ ቤተሰቦቿ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪዋ በፖሊስ እየታደነች ነው ተብሏል፡፡

የቤት ሰራተኛዋ በሟች ወ/ሮ ፋሲካ ተሾመ ቤት ውስጥ ተቀጥራ ለአንድ ዓመት ከ6 ወር መሥራቷን የጠቆሙት ቤተሰቦቿ፤ እስካሁን  ቀጣሪዋን የገደለችበት ምክንያት አለመታወቁን ነው የገለጹት፡፡የ60 ዓመቷ ሟች ወ/ሮ ፋሲካ፣ የሁለት ልጆች እናት ሲሆኑ፤ በትናንትናው ዕለት ቤታቸው ውስጥ ብቻቸውን ሳሉ ነው በቤት ሰራተኛቸው በአሰቃቂ ሁኔታ  የተገደሉት ተብሏል፡፡

ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ከፈጸመች በኋላ እቃዎቿን ሸክፋና በሟች ላይ በር ዘግታ ከአካባቢው መሰወሯን ነ ው ቤተሰቦች የገለጹት፡፡

   በምስሉ ላይ የምትታየውን ተጠርጣሪ  ወንጀለኛ በየትም ቦታ ያየ ፣ ለፖሊስ በመጠቆም በቁጥጥር ሥር እንድትውል ይተባበር ዘንድ የሟች ቤተሰቦች ተማጽነዋል፡፡

Read 12191 times Last modified on Saturday, 29 October 2022 19:03